ስፓርት
በለንደን እና ጣልያን በተካሄዱ የተለያዩ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያ አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በለንደን የማራቶን፣ በጣልያን የግማሽ ማራቶን እና የ10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድሮችን ኢትዮጵያ በበላይነት አጠናቀቀች፡፡
በለንደን የተካሄደው የሴቶች የማራቶን ውድድር በአትሌት ያለምዘርፍ የኋላው አሸናፊነት ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡
አትሌት ያለምዘርፍ እርቀቱን 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው ያሸነፈችው፡፡
በለንደን በተካሄደ የወንዶች የማራቶን ውድድር ደግሞ÷ አትሌት ልዑል ገብረ ሥላሴ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት ቀነኒሳ በቀለ አምሥተኛ በመሆን…
Read More...
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማና ባሕር ዳር ከተማ አሸነፉ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መክፈቻ ጨዋታዎች ወልቂጤ ከተማና ባሕር ዳር ከተማ ተጋጣሚዎቻቸውን በማሸነፍ የውድድር ወቅቱን በድል ጀምረዋል።
ፕሪሚየር ሊጉ ዛሬ በባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ተጀምሯል።
በሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታ ወልቂጤ ከተማ አምበሉ ጌታነህ ከበደ በ50ኛው ደቂቃ ባስቆጠረው ድንቅ የቅጣት…
የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ እየገቡ ነው
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ማኅበራት ምክር ቤት (ሴካፋ) ከ17 ዓመት በታች የእግር ኳስ ተሳታፊ ሀገራት አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ከተሳታፊ ሀገራት መካከል የብሩንዲ፣ የደቡብ ሱዳን እና ሶማሊያ ከ17 ዓመት ብሔራዊ ቡድኖች ትናንት ማምሻውን አዲስ አበባ መግባታቸውን…
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ23 ዓመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር ያደረገው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን 1ለ 0 ተሸንፏል፡፡
ቡድኑ ባሳለፍነው ሐሙስ በአበበ ቢቂላ ስታድየም ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አቻው ጋር ያደረገውን የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ ውጤት መለያየቱ…
ጀግኖቹ ከ30 ዓመት በኋላ ድል ባደረጉባት የስፔኗ ባርሴሎና ከተማ ተገናኙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) እ.ኤ.አ በ1992 የባርሴሎና ኦሎምፒክ በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች ውድድር ለአፍሪካ የመጀመሪያውን የወርቅና የብር ሜዳልያ ያስገኙት ኢትዮጵያዊቷ የአሁኑ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ደራርቱ ቱሉ እና ደቡብ አፍሪካዊቷ ኤሊና ማየር የመጀመሪያ የኦሊምፒክ ድላቸውን ባጣጣሙበት ባርሴሎና ከተማ ከ30 ዓመት በኋላ በዛሬው…
ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ሻምፒዮን ሆነ
ቅአዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለብ 16ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ (ሲቲ ካፕ) ሻምፒዮን ሆነ፡፡
የፍጻሜ ጨዋታውን ከመከላከያው እግር ኳስ ክለብ መቻል ጋር ያደረገው ቅዱስ ጊዮርጊስ በሀብቶም ገብረ እግዚያብሔር ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ነው ሻምፒዮን መሆን የቻለው።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የአዲስ…
አትሌት ትዕግስት አሰፋ በበርሊን ማራቶን የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መስከረም 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በበርሊን በተካሄደው 48ኛው የበርሊን ማራቶን አትሌት ትዕግስት አሰፋ የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፋለች፡፡
አትሌት ትዕግስት 2 ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከ37 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነው የቦታው አዲስ ክብረወሰን ያስመዘገበችው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ …