ስፓርት
ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 1፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ23ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ባህር ዳር ከነማ ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና በሞሃመድ ናስር ግብ መምራት ቢችልም ሃብታሙ ታደሰ አስቆጥሮ በአንድ አቻ ውጤት ወደ እረፍት አምርተዋል፡፡
ከእረፍት መልስ አለልኝ አዘነ በጨዋታ እንዲሁም ያሬድ ባዬ በፍፁም ቅጣት ምት ግብ አስቆጥረው በሙሉ ሰዓት ውጤት ባህር ዳር ከነማ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎም የጣና ሞገዶች ወደ ዋንጫ…
Read More...
በፕሪሚየር ሊጉ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተጠናቀቁ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 23ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
ወላይታ ድቻና አዳማ ከተማ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ባደረጉት ጨዋታ 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የአዳማ ከተማን ግብ ዮሴፍ ታረቀኝ 65ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር÷የወላይታ ድቻን ደግሞ ቢኒያም ፍቅሩ 82ኛው ላይ…
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከማላዊ ጋር በሞዛምቢክ ይጫወታል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 30፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ከማላዊ ጋር በሞዛምቢክ ሜዳ እንደሚጫወት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ፡፡
ብሄራዊ ቡድኑ 5ኛ የምድብ ጨዋታውን ሰኔ 13 ቀን የሚያደርግ ሲሆን ጨዋታውን በሞዛምቢክ ስታዲየም ለማድረግ ቀጠሮ መያዙን ለካፍ አሳውቋል፡፡
ፌዴሬሽኑ በምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በሚገኙ…
በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸንፈዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 29፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ሀገራት በተደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ትናንት በቼክ ሪፐብሊክ በተደረገ ፕራግ ማራቶን በሴቶች አትሌት ወርቅነሽ ኢዴሳ ስታሸንፍ በወንዶች አትሌት ሲሳይ ለማ ሁለተኛ ወጥቷል።
በአሜሪካ በተካሄደው ፒትስበርግ ግማሽ ማራቶን በሴቶች አትሌት ብዙዬ ድሪባ…
ሲዳማ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና ሐዋሳ ከተማን እንዲሁም ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልቂጤ ከተማን አሸነፉ፡፡
9፡00 ላይ በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሔደው ጨዋታ÷ ፍሊፕ አጃህ በሁለተኛው አጋማሽ ባስቆጠራት ብቸኛ ጎል ሲዳማ ቡና ተጋጣሚውን ረትቷል፡፡
በሌላ በኩል 12፡00 ላይ ወልቂጤ ከተማ እና ቅዱስ…
ሃላንድ የፕሪሚየር ሊጉን ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪነት ክብረ ወሰን ሰበረ
አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የማንቼስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጫዋች ኧርሊንግ ሃላንድ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዝግቧል።
የ22 አመቱ ኖርዌያዊው አጥቂ ትናንት ምሽት ክለቡ ማንቼስተር ሲቲ ከዌስትሃም ዩናይትድ ጋር ባደረገው ጨዋታ በሊጉ 35ኛ ጎሉን አስቆጥሯል።
ይህም ከዚህ ቀደም በቀድሞወቹ እንግሊዛውያን አጥቂዎች አንዲ…
በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ22ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ መቻል እና ኢትዮጵያ መድን ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡
9፡00 ላይ በተካሄደው ጨዋታ መቻል ድሬዳዋ ከተማን 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
ከነዓን ማርክነህ እና እስራኤል እሸቱ የመቻልን ሁለት ጎሎች ሲያስቆጥሩ÷ ብቸኛዋን ድሬዳዋ ጎል ሙኸዲን ሙሳ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን…