ስፓርት
ፋሲል ከነማ በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ ፣ መስከረም 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ከቡሩንዲው ቡማሙሩ ጋር የተጫወተው ፋሲል ከነማ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፉን አረጋግጧል።
ፋሲል ከነማ በዛሬው እለት በመልስ ጨዋታው 1 ለ 0 ቢሸነፍም በድምር 3ለ1 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፏል።
ባህር ዳር ላይ በተካሄደው የመጀመሪያ ጨዋታ ፋሲል ከነማ 3 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል።
ቡድኑ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ከቱኒዚያው ሴፋክሲን ጋር ይጫወታል።
Read More...
ፋሲል ከነማ ከብሩንዲው ቡማሙሩ ክለብ ጋር የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ከብሩንዲው ቡማሙሩ ክለብ ጋር የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የቅድመ-ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያደርጋል፡፡
የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ከቀኑ 10 ሰአት ላይ 10 ሺህ ተመልካች በሚያስተናግደው የታንዛንያው አዛም ኮምፕሌክስ ስታዲየም ይከናወናል።
ጨዋታው በታንዛንያ የሚደረገው ቡማመሩ የሚጫወትበት ስታዲየም…
የሴካፋ ከ17 ዓመት በታች ውድድር ድልድል ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ የወንዶች ከ17 ዓመት በታች ዋንጫ የሴካፋ ዞን የማጣርያ ውድድር የምድብ ድልድል ዛሬ ይፋ ሆኗል፡፡
ውድድሩ በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት ከመስከረም 20 እስከ ጥቅምት 5 ቀን 2015 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡
በወጣው መርሐ ግብር መሰረት ፥ በምድብ አንድ፥ ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ ፣ደቡብ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ሶማሊያ…
ፌዴሬሽኑ የአሰልጣኝ ውበቱ አባተን ውል አራዘመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ውላቸውን ለማራዘም ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ዛሬ ስምምነት ፈፅመዋል።
አሰልጣኙ ውላቸው መጠናቀቁ የተገለፀ ሲሆን ÷ይህን ተከትሎም ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት በዋና አሰልጣኝነት እንዲቀጥሉ ስምምነት መፈፀሙ ታውቋል፡፡
አሰልጣኝ ውበቱ በ2013 ዓ.ም ብሔራዊ ቡድኑን…
ባህር ዳር ከተማ ደግአረገ ይግዛውን በአሰልጣኝነት ሾመ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ደግአረገ ይግዛው የባህር ዳር ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ በመሆን ተሾሙ፡፡
የቀድሞው የክለብ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል።
ይህን ተከትሎም አሠልጣኙ ቀሪ የአንድ ዓመት ውል ቢኖራቸውም ከቡድኑ ጋር እንደማይቀጥሉ መገለፁ ይታወቃል።
ክለቡ በእርሳቸው…
የቻን ውድድር የምድብ ድልድል መስከረም 21 ቀን ይፋ ይሆናል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የምትሳተፍበት የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን (ቻን) ውድድር መስከረም 21 ቀን 2015 ዓ.ም ይፋ ይሆናል፡፡
በ2023 በአልጄሪ አስተናጋጅነት በሚከናወነው የቻን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ የተሳታፊዎችን ቁጥር ያደገ ሲሆን በ18 ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ከጥር 5 እስከ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይከናወናል፡፡…
ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾሙ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የባህርዳር ከነማ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነው ተሾመዋል።
አሰልጣኙ ፊፋ ለቴክኒክ ባለሙያነት ያቀረባቸውን መመዘኛዎች በማለፍ እንደ ሁኔታው በሚታደስ የሁለት ዓመት ኮንትራት የፊፋ የቴክኒክ ባለሙያ ሆነዋል።
ኢንስትራክተር አብርሃም በአፍሪካ ከፍተኛ ኢንስትራክተርነት ፣ በአፍሪካ…