ስፓርት
በዛምቢያ ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 22፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)በዛምቢያ ንዶላ እየተካሄደ ባለው ከ20 ዓመት በታች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
ሁለተኛ ቀኑን ባስቆጠረው ውድድር ዛሬ የ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከታትለው በመግባት አሸንፈዋል።
በዚህም አትሌት ውብርስት አስቻለ በአንደኝነት የወርቅ ሜዳሊያ ስታጠልቅ፣ አትሌት ሳምራዊት ሙሉጌታ 2ኛ በመሆን የብር እንዲሁም አትሌት ምጥን እውነቴ በሦስተኝነት የነሐስ ሜዳሊያ አግኝተዋል።
በወንዶች ደግሞ ማሞ ኢማና 2ተኛ ደረጃን በመያዝ…
Read More...
ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ድሬዳዋ ከተማን 4 ለ 1 አሸነፈ፡፡
ለኢትዮጵያ ቡና መስፍን ታፈሰ፣ ሮቤል ተክለሚካኤል፣ አንተነህ ተፈራ እና አማኑኤል ዮሐንስ ጎሎቹን ሲያስቆጥሩ ብቸኛዋን የድሬዳዋ ጎል ያሲን ጀማል አስቆጥሯል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ነጥቡን 30 በማድረስ ከሀድያ ሆሳዕና እና ፋሲል ከነማ ጋር…
ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በ21ኛ ሣምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ፡፡
9፡00 ላይ አርባምንጭ ከተማን የገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ በእስማኤል ኦሮ አጉሮ ብቸኛ ጎል 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ፈረሰኞቹ ከተከታያቸው ባሕርዳር ከተማ ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ወደ ሥድስት ማስፋት…
የፕሪሚየር ሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪዎች ፍልሚያ በኢቲሃድ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፕሪሚየርሊጉ የዋንጫ ተፎካካሪዎች ማንቼስተር ሲቲ እና አርሰናል ፍልሚያቸውን ዛሬ ምሽት ያደርጋሉ፡፡
በጨዋታው መድፈኞቹ ከተከታዩ ማንቼስተር ሲቲ ጋር ያላቸውን የነጥብ ልዩነት ለማስፋት እና ከ19 ዓመት በኋላ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
ለሦስት ዋንጫ የሚፎካከሩት ውሃ ሰማያዊዎቹ በአንፃሩ…
ለገጣፎ ለገዳዲ ከሀድያ ሆሳዕና አቻ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሣምንት ጨዋታ ለገጣፎ ለገዳዲ እና ሀድያ ሆሳዕና በአቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ዛሬ 9፡00 ላይ በአዳማ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የተካሄደው የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ያለምንም ጎል ተጠናቋል፡፡
12:00 ላይ በተካሄደ ሌላ የጨዋታ መርሐ ግብር አዳማ ከተማ ሲዳማ ቡናን…
አትሌት መገርቱ ዓለሙ እና ታምራት ቶላ በለንደን ማራቶን 2ኛ እና 3ኛ ወጡ
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሔደው የለንደን 2023 ማራቶን ከሴቶች አትሌት መገርቱ ዓለሙ 2ኛ እንዲሁም ከወንዶች አትሌት ታምራት ቶላ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቁ፡፡
በተጨማሪም በወንዶች ልዑል ገብረ ሥላሴ 4ኛ እና ሰይፉ ቱራ 5ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡
ዛሬ የተካሄደውን የማራቶን ውድድር በሴቶች አትሌት ሲፈን ሀሰን…
በፕሪሚየር ሊጉቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ድሬዳዋ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡
በዚህም 9 ሰዓት ቅዱስ ጊዮርጊስና ፋሲል ከነማ ጨዋታቸውን ያደረጉ ሲሆን÷ ቅዱስ ጊዮርጊስ 1ለ0 አሸንፏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስን…