Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አርሰናል ክሪስቲያን ሞስኬራን ማስፈረሙን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ወጣቱን ስፔናዊ ተከላካይ ክሪስቲያን ሞስኬራ ከቫሌንሲያ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ የሰሜን ለንደኑ ክለብ ለ21 ዓመቱ ተጫዋች 13 ሚሊየን ፓውንድ መነሻ የዝውውር ሂሳብ ይከፍላል፡፡ ክሪስቲያን ሞስኬራ በመድፈኞቹ ቤት ለአምስት ዓመት የሚያቆየውን ውል የፈረመ ሲሆን፥ አርሰናል ተጫዋቹን ለተጨማሪ አንድ ዓመት ማቆየት የሚችልበት ማራጭ በውሉ ተካቷል፡፡ አርሰናል በተመሳሳይ ቪክተር ጎከሬሽን ከስፖርቲንግ ሊዝበን ለማስፈረም መስማማቱ ይታወሳል፡፡
Read More...

ቪክተር ጎከሬሽ የአርሰናል ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ወደ ለንደን ሊያቀና ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 17፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አርሰናል ቪክተር ጎከሬሽን ከስፖርቲንግ ለማስፈረም ከስምምነት ላይ መድረሱን ተከትሎ ተጫዋቹ ዝውውሩን ለማጠናቀቅ ነገ ወደ ለንደን እንደሚያቀና ተነግሯል፡፡ አርሰናል ለ27 ዓመቱ ስዊድናዊ አጥቂ ዝውውር 55 ነጥብ 1 ሚሊየን ፓውንድ እና ብቃቱ እየታየ የሚጨመር 8 ነጥብ 7 ሚሊየን ፓውንድ ይከፍላል፡፡…

ሊቨርፑል ሁጎ ኢኪቲኬን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ሊቨርፑል ሁጎ ኢኪቲኬን ከኢንትራ ፍራንክፈርት ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ የ23 ዓመቱ ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጫዋች በሊቨርፑል ለስድስት ዓመታት የሚያቆየውን ኮንትራት ተፈራርሟል፡፡ ሊቨርፑል ለተጫዋቹ ዝውውር 69 ሚሊየን ፓውንድ እና እየታየ የሚጨመር 10 ሚሊየን ፓውንድ በአጠቃላይ 79 ሚሊየን ፓውንድ ወጪ…

ራሽፎርድ ባርሴሎናን ተቀላቀለ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የስፔኑ ክለብ ባርሴሎና ማርከስ ራሽፎርድን በውሰት ውል ከማንቼስተር ዩናይትድ አስፈርሟል፡፡ በዚህ መሰረትም ማርከስ ራሽፎርድ ለአንድ የውድድር ዓመት በውሰት ውል በባርሴሎና ቆይታ ይኖረዋል፡፡ ባርሴሎና በውሰት ውሉ ላይ የተቀመጠውን የመግዛት አማራጭ በመጠቀም ራሽፎርድን በቋሚነት ማስፈረም ይችላል፡፡ እንግሊዛዊው…

አትሌት ትዕግስት አሰፋ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን ትወክላለች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ትዕግስት አሰፋ በጃፓን ቶኪዮ በሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በመወከል ትወዳደራለች። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከአሠልጣኟ ጋር ባደረገው ውይይት አትሌት ትዕግስት በዓለም ሻምፒዮና ላይ ሀገሯን በመወከል እንድትሳተፍ ከስምምነት ላይ መደረሱን ገልጿል። በአሁኑ ስዓት አትሌቷ በጥሩ አቋም ላይ…

ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን የዕውቅናና የሽልማት መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በናይጄሪያ አቡኩታ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና 18 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ ተሳታፊ ለነበሩት አትሌቶችና የቡድን አባላት የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተከናውኗል፡፡ በውድድሩ ለተሳተፉ እና ሜዳሊያ ላስገኙ አትሌቶች፣ ለአሰልጣኞች፣ ለቡድን መሪ እና ለልዑካን ቡድኑ አባላት የማበረታቻ ሽልማት…

ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አገኘች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳልያ አግኝታለች፡፡ ከ18 ዓመት በታች 5 ሺህ ሜትር ሴቶች ርምጃ የፍጻሜ ውድድር አትሌት ሕይወት አምባው ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡ በናይጄሪያ አቡኩታ እየተካሄደ የሚገኘው የአፍሪካ ከ18 እና ከ20 ዓመት በታች…