Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና ወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በሀዋሳ ዩንቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው 29ኛ ሳምንት የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና በየነ ባንጃ እና ተመስገን ብርሃኑ እንዲሁም ማሞ አየለ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸንፎ ወጥቷል። ወልዋሎ አዲግራት ከሽንፈት ያልታደጉትን ግቦች ፉዓድ አዚዝ (ፍ) እና ዳዋ ሁጤሳ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
Read More...

ድሬዳዋ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የተገናኙት ድሬዳዋ ከተማ እና መቐለ 70 እንደርታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ የድሬዳዋ ከተማን ግብ ሀቢብ ከማል በፍጹም ቅጣት ምት በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ ማስቆጠር ችሏል፡፡ እንዲሁም የመቐለ 70 እንደርታን ግብ ያሬድ ብርሃኑ ወደ መልበሻ ክፍል…

ሐዋሳ ከተማ  አርባምንጭ ከተማን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሐዋሳ ከተማ አርባምንጭ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሐዋሳ ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ እስራኤል እሸቱ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ሐዋሳ ከተማ ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያሳካ፤ አርባምንጭ ከተማ ደግሞ ባለፉት ሦስት ተከታታይ ጨዋታዎች ሽንፈት…

ካርሎ አንቼሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ጣሊያናዊው ካርሎ አንቼሎቲ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በመሆን መሾማቸው ይፋ ሆኗል፡፡ ሪያል ማድሪድ ከሪያል ሶሴዳድ የሚያደርገው የላሊጋው ጨዋታም በማድሪድ ቤት የመጨረሻ ኃላፊነታቸው እንደሚሆን ተገልጿል፡፡ አንቼሎቲ በፈረንጆቹ ግንቦት 26 በይፋ የብራዚል ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነታቸውን እንደሚረከቡ ዘ አትሌቲክ…

አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ በባርሴሎና ለመቆየት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የባርሴሎናው አሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ ለተጨማሪ ሁለት ዓመታት የሚያቆያቸውን ውል ለመፈረም ከክለቡ ጋር ተስማምተዋል፡፡ ከትናንት ምሽቱ የኤል ክላሲኮ ድል በኋላ ዩዋን ላፖርታን ጨምሮ የክለቡ አመራሮች ከአሰልጣኝ ሀንሲ ፍሊክ እና ወኪላቸው ጋር መወያየታቸውን ባርካ ዩኒቨርሳል ምጮቹን ጠቅሶ  ዘግቧል፡፡ ከውይይቱ በኋላም…

ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን በማሸነፍ መሪነቱን አጠናከረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ጨዋታ ባርሴሎና ሪያል ማድሪድን 4 ለ 3 በሆነ ውጤት በማሸነፍ መሪነቱን አጠናክሯል፡፡ በጨዋታው ለባርሴሎና ራፊንሀ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል እና ኤሪክ ጋርሺያ  ቀሪዎቹን ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል፡፡ ሪያል ማድሪድን ከሽንፈት መታደግ ያልቻሉ ሶስት ግቦች ፈረንሳዊው የፊት መስመር…

ማንቼስተር ዩናይትድ 17ኛ ሽንፈቱን አስተናገደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በ2024/25 የውድድር ዘመን 17ኛ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡ በኦልድትራፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን ያስተናገደው ዩናይትድ ጃሮድ ቦውን እና ቶማስ ሱቼክ ባስቆጠሯቸው ግቦች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ በሌሎች የሊጉ 36ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ጨዋታዎች ክሪስታል ፓላስ…