Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀዋሳ ከተማ ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሀዋሳ ከተማን የማሸነፊያ ግቦች እስራኤል እሸቱ እና አሊ ሱሌማን ሲያስቆጥሩ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ቢኒያም ፍቅሬ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የሀዋሳ ከተማ የፊት መስመር ተጨዋች አሊ ሱሌማን በውድድር ዓመቱ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 13 ከፍ በማድረግ ኮከብ ጎል አስቆጣሪነቱን መምራቱን ቀጥሏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ ከተማ በ37 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ40…
Read More...

ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ30ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሲዳማ ቡና ወላይታ ድቻን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ ማይክል ኪፕሩቪል በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ሲዳማ ቡና ተከታታይ ሁለተኛ ድሉን ሲያስመዘግብ ወላይታ ድቻ በበኩሉ ሁለተኛ ተከታታይ ሽንፈቱን አስተናግዷል፡፡…

ክሪስቲያኖ ሮናልዶ ለተከታታይ 3ኛ ዓመት የዓለማችን ቁጥር አንድ ተከፋይ ስፖርተኛ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የ40 ዓመቱ ፖርቹጋላዊ ኢንተርናሽናል ለተከታታይ ለሦስተኛ ዓመት የዓለማችን ቁጥር አንድ ተከፋይ ስፖርተኛ መሆን ችሏል፡፡ በአሁኑ ወቅት ለሳዑዲው ክለብ አልናስር እየተጫወተ የሚገኘው ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፤ በዓመት 275 ሚሊየን ዶላር የሚከፈለው የምድራችን ቁጥር አንድ ስፖርተኛ መሆኑን የፎርብስ መጽሔት መረጃ አመላክቷል፡፡…

ሰርጂም ራትክሊፍ ከ6 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ከሰሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የማንቼስተር ዩናይትድ አነስተኛ ድርሻ ባለቤት ሰር ጂም ራትክሊፍ በአንድ ዓመት ውስጥ ከ6 ቢሊየን ፓውንድ በላይ ከስረዋል፡፡ እንግሊዛዊው ባለሀብት ሰር ጂም ራትክሊፍ ሀብታቸው ከ23 ነጥብ 519 ቢሊየን ፓውንድ ወደ 17 ነጥብ 046 ቢሊየን ፓውንድ ገደማ ዝቅ ማለቱን ቢቢሲ ዘግቧል። የ72 ዓመቱ ባለሃብት ባለፉት 12…

ሸገር ከተማ የመላው ኦሮሚያ ስፖርት ውድድር አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከሚያዝያ 26 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በአምቦ ከተማ ሲካሄድ የነበረው የመላው ኦሮሚያ የስፖርቶች ውድድር ዛሬ ተጠናቅቋል። በውድድሩ ከ8 ሺህ በላይ ስፖርተኞች በ20 የስፖርት ዓይነቶች መሳተፋቸው ተገልጿል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አወሉ አብዲ፤ ውድድሩ በርካታ ማኅበረሰቦችን በአንድ አሰባስቦ የሚደረግ…

ቼልሲ ከማንቼስተር ዩናይትድ….

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቼልሲ በሜዳው ስታምፎርድ ብሪጅ ምሽት 4 ሠዓት ከ15 ላይ ማንቼስተር ዩናይትድን ያስተናግዳል። በ63 ነጥብ 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ ለሚቀጥለው የውድድር ዘመን የሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ቦታን ለማግኘት በሚደረገው ፉክክር ውስጥ ለመቆየት ይፋለማል።…

በፕሪሚየር ሊጉ መቻል እና ስሑል ሽረ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሣምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የተገናኙት መቻል እና ስሑል ሽረ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡ 12 ሠዓት ላይ በተካሄደው ጨዋታ የመቻልን ግብ ሽመልስ በቀለ ሲያስቆጥር፤ የስሑል ሽረን ደግሞ ኤልያስ አሕመድ በፍጹም ቅጣት ምት ከመረብ አሳርፏል፡፡ ቀደም ብሎ በተካሄደ የዕለቱ የመጀመሪያ መርሐ ግብር፤…