Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 7፣2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመንግሥትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል እንደሚከናወን ተገለፀ። የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ የሺዋስ አለሙ ፥ መንግስት በትግራይ ክልል ህግን ለማስከበር እያደረገ ላለው ተግባር ለመንግሥትና ለሀገር መከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚሆን ማህበረሰብ አቀፍ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ጨምሮ የደም ልገሳ እና የገንዘብ ድጋፍ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ይከናወናሉ፡፡ የድጋፉ መርሃ ግብር በጋሞ እና ስልጤ ዞን ከፍተኛ የስራ…
Read More...

በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በቶኪዮ 2020 ኦሊምፒክ የተሳተፈው የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን ዛሬ ጠዋት አቀባበል ተደርጎለታል:: ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው አቀባበል የተደረገለት ። ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦…

ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ብራዚል በቶኪዮ ኦሊምፒክ የወንዶች እግር ኳስ አሸናፊ ሆነች። በፍጻሜው ከስፔን ጋር የተገናኘችው ብራዚል ጨዋታውን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፋለች። መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ አንድ አቻ የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በተጨማሪ 30 ደቂቃዎች ብራዚል ተጨማሪ ጎል አስቆጥራ የውድድሩ አሸናፊ ሆናለች። ለብራዚል የድል ጎሎቹን…

ጠ/ሚ ዐቢይ በአትሌት ለተሰንበት ግደይ በተመዘገበው ውጤት የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ በሴቶች 10 ሺህ ሜትር የሩጫ ውድድር በአትሌት ለተሰንበት ግደይ የነሐስ ሜዳሊያ በማግኘቷ የእንኳን ደስ አለን መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ለወንዶች ማራቶን ተወዳዳሪዎቻች መልካም ዕድል ተመኝተዋል፡፡…

የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብን ለማጠናከር ያለመ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብን ህዝባዊ መሠረት ለማስያዝና የገንዘብ አቅሙን ለማጠናከር በአርባ ምንጭ ከተማ የጎዳና ላይ ሩጫ ተካሄደ ። ክለቡ በ2014 ዓ.ም በሚደረገው የቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ተፎካካሪ እንዲሆን ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑም ተጠቁሟል። የአርባ ምንጭ ከነማ ስፖርት ክለብ…

አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኘች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 1 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ 10 ሺህ ሜትር የሴቶች የሩጫ ውድድር አትሌት ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳልያ አስገኝታለች። አትሌት ለተሰንበት ውድድሩን 3ኛ በመሆን አጠናቃለች። በውድድሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሃሰን 1ኛ ስትሆን ሌላኛዋ ትውልደ ኢትዮጵያዊት ቃል ኪዳን ገዛኸኝ 2ኛ በመሆን ውድሯን አጠናቃለች።

በቶኪዮ ኦሊምፒክ 1500 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ ኦሊምፒክ 1500 ሜትር ሴቶች ውድድር የተሳተፈችው አትሌት ፍሬወይኒ ሃይሉ 4ኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቃለች፡፡ በውድድሩ ኬንያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን የኦሎምፒኩን ሪከርድ በመስበር ስታሸንፍ እንግሊዛዊቷ አትሌት ሙዪር ሁለተኛ ወጥታለች፡፡ እንዲሁም ለኔዘርላንድ የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲፋን ሀሰን…