Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ዋልያዎቹ  ኮትዲቯር አቢጃን ደረሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ወንዶች ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ኮትዲቯር አቢጃን ደርሰዋል። ዋሊያዎቹ ከ5 ሰዓት የአየር በረራ በኋላ አቢጃን አየር ማረፊያ ሲደርሱ በኮትዲቫር የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ሙሉጌታ እና በኤምባሲው ሰራተኞች እንዲሁም በኢትዮጵያ አየር መንገድ የአቢጃን ተወካዮች አቀባበል ተደርጎላቸዋል። ብሔራዊ ቡድኑ በአቢጃን ሴን ሆቴል ማረፊያውን ማድረጉን ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ በመጪው ማክሰኞ ከኮትዲቫር ብሄራዊ ቡድን ጋር…
Read More...

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ከደቡብ አፍሪካዊው አሰልጣኝ ማሂር ዴቪድስ ጋር በስምምነት የተለያየው ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማኅበር  አሰልጣኝ ፍራንክ ናፓልን ዋና አሰልጣኝ አድርጎ ሾሟል፡፡ አሰልጣኝ ፍራንክ በእግር ኳሱ ዘርፍ ከ35 ዓመታት በላይ በተለይ በአፍሪካ በማሰልጠን ልምድ ያካበቱና ውጤታማ መሆን የቻሉ መሆናቸውን እግር ኳስ ማህበሩ በፌስቡክ ገፁ…

ጠ/ሚ ዐቢይ ለዋልያዎቹ መልካም ውጤት ተመኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) መልካም ውጤት ተመኙ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማለፍ ዕድሉን አስፍቷል ሲሉ አስፍረዋል። ከተለያዩ አካባቢዎች እና ቡድኖች የመጡ ተጨዋቾች በአንድ ዓላማ ተጫውተው…

የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)  “የዩኒቨርስቲ ስፖርት ዓለምን ለመቀየር” በሚል መሪ ቃል የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ፌዴሬሽን አጠቃላይ ስብሰባ በኮተቤ ሜትሮፓሊታን ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤና የተለያዩ ከአፍሪካ ሀገራት የመጡ የፌዴሬሽኑ አባላት…

ደሴቷ ሀገር ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ደሴቷ ሀገር እና 900 ሺህ ህዝብ ብቻ ያላት ኮሞሮስ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ  ለአፍሪካ ዋንጫ ማለፏን አረጋገጠች። ከቶጎ ብሄራዊ ቡድን ጋር 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት መለያየቷን ተከትሎ ደሴቷ ሀገር በካሜሩን አዘጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ አልፋለች። 5 ጨዋታዎችን አድርጋ 9 ነጥብ በመሰብስ በምድቧ በግብ ክፍያ…

ዋልያዎቹ ማዳጋስካርን 4 ለ 0 በማሸነፍ የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የወንዶች ብሄራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ማዳጋስካርን 4 ለ0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። በባህርዳር ዓለም አቀፍ ስታድየም በተካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ዋልያዎቹ ኮቲዲቫር ከኒጀር የሚያደርጉት ጨዋታ ውጤት እስከሚታወቅ የደረጃ ሰንጠረዡን በ9 ነጥብ መምራት ጀምረዋል። ግቦቹን…

ቻድ ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ታገደች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቻድን ከ2021ዱ የአፍሪካ እግር ኳስ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር ማገዱን አስታወቀ፡፡ ካፍ ውሳኔውን ያስተላለፈው የሀገሪቱ መንግስት የቻድን እግር ኳስ ማህበር በይፋ ማፍረሱን ተከትሎ ነው፡፡ የቻድ ብሄራዊ ቡድን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከናሚቢያ እሁድ ደግሞ ከማሊ ጋር የነበረውን ጨዋታ…