Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በቻምፒየንስ ሊጉ ሪያል ማድሪድ እና ማንቼስተር ሲቲ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቀሉ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 8፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ትናንት ምሽት ሁለት ጨዋታዎች ተካሄደዋል፡፡ ማንቼስተር ሲቲ ቦሩሲያ ሞንቼግላድባህን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ፥ ኬቪን ደብሩይነ እና ኢካይ ጉንዶኻን የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡ በደርሶ መልስ ውጤት ማንቼስተር ሲቲ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል፡፡ በሌላ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አታላንታን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ካሪም ቤንዜማ፣ ሰርጂዮ ራሞስ እና ማርኮ አሴንሲዮ የማሸናፊያ ጎሎቹን ለሪያል ማድሪድ ሲያስቆጥሩ፥…
Read More...

የዋና ስፖርት ዳኛ ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አንጋፋው የውሃ ዋና ስፖርት ዳኛ ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ በኢትዮጵያ ውሃ ዋና ስፖርት ውስጥ በዳኝነትና በአሰልጣኝነት ለረጅም ጊዜ ያገለገሉት ኢንስፔክተር ሲሳይ ወየሳ ዛሬ በድንገት ሕይወታቸው ማለፉን የኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን አስታውቋል። ኢንስፔክተር ሲሳይ የኦሮሚያ ፖሊስ ባልደረባ የነበሩ…

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ ሃብቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ሩጫ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን የሚገኙ ተፈጥሯዊ ሃብቶችን ለማስተዋወቅ ያለመ ሩጫ በሮቤ ከተማ ተካሂዷል፡፡ ውድድሩ በክልሉ ቱሪዝም ኮሚሽን መዘጋጀቱ የተገለፀ ሲሆን ምክትል ኮሚሽነር አቶ አቢዩ ተሰማ ውድድሩ ዞኑ ያለውን ሃብት ለማስተዋወቅ ታስቦ ተዘጋጀ ነው ብለዋል፡፡ በቀጣይም ቱሪዝሙን ለማስተዋወቅ…

10ኛው አባይ ናይል ማራቶን ህዝባዊ የሩጫ ውድድር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው አባይ ናይል ማራቶን ህዝባዊ የሩጫ ውድድር በባህርዳር ከተማ ተካሄደ፡፡ በውድድሩ አንጋፋና ተተኪ አትሌቶች ከአዲስአበባ ፣ከአማራ ክልል እንዲሁም ከሌሎች ክልሎች መሳተፋቸውን የውድድሩ አዘጋጅ አትሌት መልካሙ ተገኘ ተናግረዋል፡፡ ውድድሩ ተተኪ አትሌቶች ለማፍራት ፣የአባይ ናይል ሩጫን ለአለም…

የፕሪሚርየር ሊጉ የውድድር ዘመኑ ፈጣን ግቦች የተመዘገቡበት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የውድድር ዘመኑ ፈጣን ግቦች የተመዘገቡበት ድሬዳዋ ከተማን ከኢትዮጵያ ቡና ያገናኘው ጨዋታ በቡናማዎቹ 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። በጨዋታውና በውድድር ዘመኑ ፈጣን የሆነውን ግብ አቡበከር ናስር በ2ኛው ደቂቃ ላይ ሲያስቆጥር ጁኒያስ ናንጄቦ ድሬዳዋን አቻ ያደረገችና የውድድር ዘመኑ…

ቢሊየነሩና የማሜሎዲ ሰንዳውን ክለብ ባለቤት ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቢሊየነሩና የማሜሎዲ ሰንዳውን ክለብ ባለቤት ፓትሪስ ሞትሴፔ የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ሆኑ። 43ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ፌዴሽን ጠቅላላ ጉባኤ በሞሮኮ ራባት በተካሄደበት ወቅት ነው ፓትሪስ ሞትሴፔ የተመረጡት። የፌዴሬሽኑ ታሪክ 7ኛው ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት ቢሊየነበሩ ፓትሪስ ሞትሴፔ በጠቅላላ…

ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዋሳ ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዋሳ ከነማ 1 ለ1 በሆነ ውጤት አቻ ተለያይተዋል፡፡ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 16ኛ ሳምንት ዛሬ ረፋድ ቅዱስ ጊዮርጊስና ሀዋሳ ከነማን አገናኝቷል፡፡ ጨዋታውም 1 ለ1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስን ግብ ጌታነህ ከበደ ሲያስቆጥር የሃዋሳን…