Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፈረንሳይ የቤት ውስጥ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ጌትነት ዋለ እና አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በፈረንሳይ በተካሄደ የቤት ውስጥ ውድድር አሸናፊ ሆነዋል፡፡ አትሌት ጌትነት ዋለ በ1 ሺህ 500 ሜትር መሰናክል ውድድር 3 ደቂቃ ከ35 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸናፊ ሆኗል፡፡ አትሌት ለሜቻ ግርማ ደግሞ ውድድሩን ሁለተኛ በመሆን አጠናቋል፡፡ በሴቶች የ800 ሜትር ውድድር ደግሞ አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ ርቀቱን 1 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ52 ማይክሮ ሰከንድ በመጨረስ አሸናፊ ሆናለች፡፡ ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ…
Read More...

ለ20 የአትሌቲክስ ዳኞች 1ኛ ደረጃ የዓለም አትሌቲክስ ሰርተፊኬት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ20 የአትሌቲክስ ዳኞች የአንደኛ ደረጃ የዓለም አትሌቲክስ ሰርተፊኬት ተሰጠ፡፡ ሰርተፊኬቱ ሲሰጥ በኢትዮጵያ የአትሌቲክስ ዳኝነት ታሪክ ለ3ኛ ጊዜ መሆኑን የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ገልጿል፡፡ የአትሌቲክስ ዳኞቹ ከሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ናቸው ተብሏል፡፡ የፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ…

በጎንደር 2ኛው አገር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በደማቅ ሁኔታ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር 2ኛው አገር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በደማቅ ሁኔታ ተካሄዷል። 2ኛው አገር አቀፍ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች በድምቀት መካሄዱን ቀጥሏል። በጎንደር ከተማ በተካሄደው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙን ተገኝተዋል፡፡ እንዲሁም በምክትል…

ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በመቀሌ ከተማ ከ50 ሺህ በላይ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ማህበር በመቀሌ ከተማ ለሚገኙ ተማሪዎች ከ50 ሺህ በላይ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ። የስፖርት ማህበሩ ተወካዮች ቡድን የተለያዩ የትምህርት መማሪያ ቁሳቁሶችን  በከተማው በመገኘት  ለከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ለአቶ አታክልቲ ኃይለሥላሴ  አስረክበዋል ። ድጋፉን የተረከቡት ከንቲባው  የቅዱስ…

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርት በሁሉም ስፍራ እንዲደርስ እየተሰራ ነው  – የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ስፖርት በሁሉም ስፍራ ደርሶ አብሮነትን ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን የኢፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን ገለጸ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስፖርት ኮሚሽን ከሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጋር በመተባበር “አብሮነታችን ለሀገራችን “በሚል መሪ  ሀሳብ ዛሬ በደብር ብርሃን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄዷል።…

በውሃ ስፖርቶች ሲሰጥ  የቆየው የአንደኛ  ደረጃ   የአሰልጣኝነት  ስልጠና  ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ  ውሃ  ስፖርቶች ፌዴሬሽን ከኦሮሚያ  ውሃ ዋና ስፖርቶች  ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር  ከጥር 26 እስከ የካቲት  4 ቀን 2013 ዓ. ም በኦሮሚያ  ክልል በቢሾፍቱ ከተማ ሲሰጥ  የቆየው የአንደኛ  ደረጃ   የአሰልጣኝነት  ስልጠና  ተጠናቀቀ። ስልጠናው በንድፈ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ሲሆን 24 ወንዶች እና 2…

ድሬዳዋ ከተማ ከአሰልጣኙ ጋር ተለያየ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድሬዳዋ ከተማ ዋና አሰልጣኝ በመሆን ሲመሩ ከቆዩት ፍስሐ ጥዑመልሳን ጋር ተለያይቷል፡፡ ድሬዳዋ ከተማን ዋና አሰልጣኝ በመሆን ያለፉት ወራትን ቡድኑን እየመሩ የቆዩት አሰልጣኝ ፍስሐ ጥዑመልሳን በዛሬው ዕለት ከክለቡ ጋር በስምምነት ተለያይተዋል። ከ2010 ጀምሮ ለድሬዳዋ ከተማ ምክትል አሰልጣኝ በመሆን ሲሰሩ የቆዩት…