ስፓርት
የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፣መጋቢት 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከአለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡
ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡
በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ…
Read More...
በዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ 4ኛ የወርቅ ሜዳሊያዋን በሳሙኤል ተፈራ አግኝታለች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር በመጨረሻው ቀን ከምሽቱ 2፡35 ላይ በተካሄደው የ1 ሺህ 500 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሩጫ ሳሙኤል ተፈራ አንደኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝቷል።
ቀደም ብሎ በተካሄደ የ800 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ ሩጫ ፍረወይኒ ኃይሉ 2ኛ በመሆን የብር…
ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያው ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር ተጫውቷል፡፡
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ከዩጋንዳ አቻቸው ጋር አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
ይህን ተከትሎም ከሜዳው ውጭ ባስቆጠራቸው ሁለት ጎሎች በዓለም ዋንጫ…
አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ የግማሽ ማራቶን የጎዳና ሩጫ ውድድር አሸነፈች
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ ኒውዮርክ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን የጎዳና ሩጫ ውድድር አሸነፈች፡፡
አትሌት ሰንበሬ ተፈሪ በኒውዮርክ ከተማ በተካሄደው ዩናይትድ ኤርላይንስ የግማሽ ማራቶን የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር አሸንፋለች።
አትሌቷ የግማሽ ማራቶን የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 1 ሰዓት ከ7 ደቂቃ…
በቤልግሬድ የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና አትሌት ሰለሞን ባረጋ በ3 ሺህ ሜትር አሸናፊ ሆኗል
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 11 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰርቢያ ቤልግሬድ እየተካሄደ ባለው የቤት ውስጥ የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።
በወንዶች 3 ሺህ ሜትር የተወዳደሩት አትሌት ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ፥ የወርቅና ብር ሜዳሊያዎች ለሃገራቸው አስገኝተዋል።
አትሌት ሰለሞን ርቀቱን 7 ደቂቃ ከ41 ሰከንድ ከ38…
ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታውን ዛሬ ያካሂዳል
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫ ማጣሪያ አንደኛ ዙር የመልስ ጨዋታ ዛሬ ከዩጋንዳ ጋር ያካሂዳል፡፡
የመልስ ጨዋታው ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይካሄዳል መባሉን ከእግር ኳስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመጀመርያው ጨዋታ ዩጋንዳ ላይ ሁለቱ…
በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጁ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤልግሬድ በ18ኛው የዓለም የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድር ምሽት 4:35 ላይ በሴቶች ምድብ የተደረገው የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ድል ተቀዳጅተዋል።
በ1 ሺህ 500 ሜትር ሴቶች የፍጻሜ ውድድር አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3 ደቂቃ ከ57 ሰከንድ ከ19 ማይክሮ…