ስፓርት
ኢትዮጵያ ቡና ኢትዮጵያ መድንን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ31ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድንን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡
የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ራምኬል ጀምስ በመጀመሪያው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ ስድስት ዝቅ ማድረግ ችሏል፡፡
ኢትዮጵያ ቡና ባለፉት አምስት የሊጉ ጨዋታዎች ድል ሲያደርግ ኢትዮጵያ መድን ከሁለት ተከታታይ ጨዋታ ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡
ውጤቱን…
Read More...
ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች የተሳተፉበት የመላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደሴ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 9ኛው መላው አማራ ጨዋታዎች ውድድር በዛሬው ዕለት ተጠናቋል።
ከግንቦት 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ “ስፖርት ለሰላም፤ ሰላም ለሁሉም” በሚል መሪ ሐሳብ ሲካሄድ በቆየው ውድድር÷ በ19 የስፖርት አይነቶች ከ18 ዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ5 ሺህ በላይ ስፖርተኞች መሳተፋቸው ተገልጿል።…
ሃሪ ኬን እና ዋንጫ የታረቁበት የውድድር ዓመት…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአርሰናል አካዳሚ ተጫዋች በነበረበት ወቅት የስፖርት አቋም የለህም ተብሎ ተባርሯል፡፡
የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን የምንጊዜም ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ነው፡፡ በፕሪሚየር ሊጉ ከአለን ሺረር በመቀጠል ሁለተኛ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ቢሆንም በሊጉ በቆየባቸው ዓመታት ግን ከዋንጫ ጋር መገናኘት አልቻለም።
በቶተንሃም ሆትስፐር…
የኢትዮጵያ አትሌቶች ከትራክ ወደ ጎዳና ውድድሮች ፍልሰት …
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ ወጣት አትሌቶች ወደ ጎዳና ውድድሮች እያመሩ መሆናቸው አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የዘርፉ ምሁራን ገለጹ።
በኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ መምህርና የአትሌቲክስ አሰልጣኝ ንጉሴ ጊቻሞ ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ አትሌቶች በትራክ ውድድሮች ላይ ራሳቸውን በሚገባ…
የፍጻሜ ተፋላሚዎቹ ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር …
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐርን ያገናኘው ተጠባቂው የዩሮፓ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4 ሠዓት ላይ በቢልባኦ ከተማ በሚገኘው ሳን ማሜስ ስታዲየም ይደረጋል፡፡
በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ወጥ ብቃት ማሳየት የተሳነው ማንቼስተር ዩናይትድ፤ በዩሮፓ ሊግ አንድም ጨዋታ ሳይሸነፍ…
ማንቼስተር ሲቲ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ቦታን ለማግኘት….
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሣምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሀድ ምሽት 4 ሠዓት ላይ ቦርንማውዝን ያስተናግዳል።
የውድድር ዓመቱን ያለ ምንም ዋንጫ ያጠናቀቀው ማንቼስተር ሲቲ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በሻምፒየንስ ሊግ የሚያሳትፈውን ቦታ ለማግኘት እየተፋለመ ይገኛል።
በአሰልጣኝ ፔፕ ጓርዲዮላ የሚመራው…
የዋንጫው መዳረሻ ያልታወቀው የጣልያን ሴሪ ኤ…
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ አምስቱ ታላላቅ ሊጎች ከጣልያን ሴሪ ኤ ውጪ አሸናፊዎቻቸውን ለይተዋል።
የጣልያን ሴሪ ኤ የዋንጫውን መዳረሻ ያላገኘ ብቸኛው የአውሮፓ ታላቅ ሊግ ሆኖ እስከመጨረሻው ሳምንት በአጓጊነቱ ቀጥሏል።
የጣልያን ሴሪ ኤ በዚህ የውድድር ዓመት ኢንተር ሚላን እና ናፖሊን ለስኩዴቶ ክብር አፋጦ የመጨረሻው ሳምንት ላይ…