Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሊቨርፑል መሪነቱን የሚያጠናክር ድል አስመዘገበ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር አንፊልድ ላይ ዎልቭስን ያስተናገደው ሊቨርፐል 2 ለ 1 በማሸነፍ ነጥቡን 60 በማድረስ መሪነቱን አጠናክሯል። ሊቨርፑል በሜዳው እና በደጋፊው ፊት ባደረገው በዚህ ጨዋታ በደረጃ ሰንጠረዡ በሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው አርሰናል ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ያሰፋበትን ውጤት ማስመዝገብ ችሏል። በሉዊስ ዲያዝ እና ሞሃመድ ሳላህ ግቦች 2 ለ 0 እየተመሩ የመጀመሪያውን አጋማሽ የጨረሱት ዎልቭሶች ከእረፍት መልስ ተጭነው በመጫወት ነጥብ ይዘው…
Read More...

አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ በካስትሎ 10 ኪሎ ሜትር ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስፔን ካስትሎ በተካሄደው የ10 ኪሎ ሜትር የወንዶች ውድድር አትሌት ዮሚፍ ቀጄልቻ አሸንፏል፡፡ አትሌት ዮሚፍ ርቀቱን 26 ደቂቃ ከ3 ሰከንድ በመግባት ነው በቀዳሚነት ማጠናቀቅ የቻለው፡፡ በውድድሩ ዮሚፍ የራሱን የ10 ኪሎ ሜትር እና የቦታውን ምርጥ ሰዓት ማስመዝገቡን የአዘጋጅ ኮሚቴው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሰሜን ኮሪያው መሪ ሶስት የፕሪሚየር ሊጉ ክለቦች በሀገራቸው እንዳይታዩ አገዱ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ቶተንሃም ሆትስፐር፣ ዎልቭስ እና ብረንትፎርድ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን እንዳይታዩ ማገዳቸው ተገለፀ፡፡ ኪም ጆንግ ኡን ትዕዛዙን የሰጡት በሶስት ክለቦች የሚጫዎቱ የደቡብ ኮሪያ ተጫዋቾችን የሰሜን ኮሪያ ዜጎች እንዳይመለከቷቸው ለማድረግ ነው ተብላል፡፡ የቶተንሃም አምበል እና አጥቂ ሰን ሁንግ…

አትሌት ድርቤ በሊዮን 3 ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንሳይ ሊዮን በተካሄደው የ3 ሺህ ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር አትሌት ድርቤ ወልተጂ ድል ቀንቷታል። ድርቤ ርቀቱን በ8 ደቂቃ 39 ሰከንድ ከ49 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው ቀዳሚ የሆነችው፡፡ አትሌቷ  ያስመዘገበችው ሰዓት የቦታው ፈጣን ሰዓት ሆኖ መመዘገቡም ተጠቁሟል፡፡ ሌላኛዋ አትሌት የኔዋ ንብረት…

ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 25ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። በውድድር ዓመቱ ደካማ እንቅስቃሴ እያሳዩ የሚገኙት ቶተንሃሞች እና ማንቼስተር ዩናይትዶች ዛሬ ምሽት 1:30 ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ ወገብ ዝቅ ብለው በ14ኛ…

ማንቼስተር ሲቲ ኒውካስል ዩናይትድን በሰፊ የጎል ልዩነት አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ25ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኒውካስል ዩናይትድን አስተናግዶ 4 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ለማንቼስተር ሲቲ በጥር የዝውውር መስኮት ክለቡን የተቀላቀለው ግብጻዊው ኦማር ማርሙሽ ሶስት ግቦችን በማስቆጠር ሃትሪክ ሲሰራ ማካቴ…

መድፈኞቹ ሌስተር ሲቲን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ወደ ኪንግ ፓወር ስታዲየም አቅንቶ ሌስተር ሲቲን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡ የመድፈኞቹን ሁለቱንም ግቦች ተቀይሮ ወደ ሜዳ የገባው ስፔናዊው ሚኬል ሜሪኖ አስቆጥሯል፡፡ አርሰናል ድሉን ተከትሎ በደረጃ ሰንጠረዡ ከመሪው ሊቨርፑል ያለውን ልዩነት በ4 ነጥብ በማጥበብ…