ስፓርት
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 2 ለ 0 ተሸንፏል፡፡
በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የታንዛኒን ብሔራዊ ቡድን ሳይመን ሀፒጎድ ምሱቫ እና ፋይሰል ሳሉም አብደላ ባስቆጠሯቸው ጎሎች አሸንፎ ወጥሯል።
በውጤቱ መሰረትም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከአምስት የማጣሪያ ጨዋታዎች በአራቱ ተሸነንፎ፣ በአንድ ጨዋታ ነጥብ ተጋርቶ 10 ጎሎች ተቆጥረውበት ከ2025ቱ የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ውጭ ሆኗል፡፡
Read More...
ኢትዮጵያ ከታንዛኒያ ዛሬ ጨዋታዋን ታደርጋለች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2025 የሞሮኮ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ አምስተኛ የምድብ ጨዋታ ኢትዮጵያ ታንዛንያን ትገጥማለች።
ጨዋታው ምሽት 1 ሠዓት ላይ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሚገኘው ስታድ ደ ማርትየርስ ስታዲየም ይደረጋል።
ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን በጄክ ፖውል ተሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 7፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ አሜሪካዊ የከባድ ሚዛን ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ጄክ ፖውል ጋር ባደረገው ግጥሚያ ተሸንፏል፡፡
ታይሰን ዛሬ ማለዳ ያደረገው ግጥሚያ ራሱን ከፕሮፌሽናል ውድድር ካገለለ ከ19 ዓመታት በኋላ የተከናወነ ነው፡፡
የግጥሚያውን ውጤት ተከትሎም ታይሰን 20 ሚሊየን እና ጄክ ፖውል 40 ሚሊየን ዶላር…
ፖል ፖግባ በ2025 ወደ ሜዳ ይመለሳል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ፈረንሳዊው አማካይ ፖል ፖግባ ከቅጣት መልስ በፈረንጆቹ 2025 ወደ እግር ኳስ ሜዳ እንደሚመለስ ተገለፀ፡፡
የ31 ዓመቱ አማካይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ወደ ጁቬንቱስ ካቀና በኋላ የተከለከለ ንጥረ ነገር ተጠቅሞ መገኘቱን ተከትሎ ለአራት አመታት በማንኛውም ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ እንዳይሳተፍ ቅጣት ተላልፎበታል፡፡
ሆኖም…
ተጠባቂው የዛሬ ምሽት የቦክስ ፍልሚያ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 6፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የ58 ዓመቱ ቦክሰኛ ማይክ ታይሰን ከ27 ዓመቱ ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ ጄክ ጆሴፍ ፖል ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ዛሬ ምሽት በአሜሪካ ቴክሳስ አርሊንግተን ይካሄዳል፡፡
ከዓመታት በፊት ቀጠሮ በተያዘለት ፍልሚያ የዓለም የቦክስ ባለታሪኩ ማይክ ታይሰን እና በ1997 ማይክ ታይሰን ልደቱን ካከበረለት ፕሮፌሽናል ቦክሰኛ እና ዩቲዩበር ጄክ…
አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ የ2024 ተስፋ ከሚጣልባቸው ሦስት ሴት አትሌቶች ውስጥ ተካተተች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 3፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ የ2024 ተስፋ ከሚጣልባቸው ሦስት ሴት አትሌቶች ውስጥ ተካትታለች፡፡
በዘንድሮ የዓለም አትሌቲክስ ምርጥ ከ20 ዓመት በታች ወይንም ተስፋ የሚጣልባቸው አትሌቶችን የዓለም አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስተዋውቋል፡፡
በዚህም አትሌት ሲምቦ ዓለማየሁ በሴቶች የ2024 ተስፈኛ ኮከብ አትሌት ሽልማት የመጨረሻ ሦስት…
ሩድ ቫኒስትሮይ ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያየ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 2፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሆላንዳዊው የቀድሞ የእግር ኳስ ኮከብ ሩድ ቫን ኒስትሮይ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር በይፋ ተለያይቷል፡፡
የ48 ዓመቱ የቀድሞ የማንቼስተር ዩናይትድ ኮከብ በሁለት ዓመት የኮንትራት ውል የማንቼስተር ዩናይትድ ምክትል አሰልጣኝ ለመሆን መስማማቱ ይታወሳል፡፡
የአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግን ስንብት ተከትሎም ቫን ኒስትሮይ ማንቼስተር…