ስፓርት
ማቼስተር ሲቲ ዎልቭስን 2 ለ 1 አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ8ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ወደ ሞሊኒክስ ስታዲየም አቅንቶ ከዎልቭስ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ማንቼስተር ሲቲ 2 ለ 1 አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ዎልቭስን ቀዳሚ ያደረገችውን ግብ ኖርዌጂያኑ ስትራንድ ላርሰን ሲያስቆጥር÷ የውኃ ሰማያዊዮቹን ግቦች ክሮሽያዊው ጆስኮ ግቫርዲዮል እና ጆን ስቶንስ ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
የፕሪሚየር ሊጉ የዛሬ መርሐ-ግብር ሲቀጥል ምሽት 12 ከ30 ላይ ሊቨርፑል ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
Read More...
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ የታዳጊ ወንዶች ጥንድ ውድድር ጃፓንና ሕንድን አሸንፋ ወርቅ አገኘች
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፍ የሜዳ ቴኒስ የታዳጊ ወንዶች ጥንድ ውድድር ኢትዮጵያ ጃፓን እና ሕንድን በማሸነፍ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች፡፡
ይህ ውድድር በዘርፉ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ ያገኘችበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
በውድድሩም ዳዊት ሸለመ እና ዳዊት ፍስሐ 64/25 እና 10/5 በሆነ ውጤት ማሸነፋቸውን የባህልና ስፖርት…
በአካል፣ በመንፈስ እና ሥነ-ልቦና ብቁ ዜጋ ለማፍራት ያለመ ንቅናቄ ማስጀመሪያ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአካል፣ በመንፈስ እና ሥነ-ልቦና ብቁ እንዲሁም ባለራዕይ ጀግና ዜጋ ለመገንባት ከፍተኛ ሚና እንዳለው የተነገረለት ንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር በወዳጅነት ዐደባባይ ተካሂዷል፡፡
የንቅናቄውን ማስጀመሪያ ያዘጋጁት የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ፣ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ እና ሄኖክ ኪዳነወልድ ስፖርት…
በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምስተርዳም ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡
አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው በአምስተርዳም ሴቶች ማራቶን የቦታውን ክብረወሰን በማሻሻል በቀዳሚነት አጠናቅቃለች፡፡
አትሌቷ ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ50 ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው የቦታውን ክብረወሰን ማሻሻል የቻለችው፡፡
በተመሳሳይ…
በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሊቨርፑልና ቸልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 8ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ተጠባቂ ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡
በዚህ መሰረትም ማንቸስተር ሲቲ ወደ ሞሊኒዮ ስታዲየም አቅንቶ ዎልቭስን ቀን 10 ሰዓት ላይ ይገጥማል፡፡
በሌላ በኩል ሊቨርፑል በሜዳው አንፊልድ ሮድ ቸልሲን 12፡30 ላይ የሚያስተናግድበት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በጨዋታው…
የካፍ ቀጣናዊ የእግር ኳስ ማህበራት ስብስባ ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን ቀጣናዊ የእግር ኳስ ማህበራት ስብስባ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
ስብስባው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ጠቅላላ ጉባዔ ጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡
ከጉባዔው ጎን ከጎን የተለያዩ ሁነቶች…
የካፍ ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 10፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ፕሬዚዳንት ፓትሪስ ሞትሴፔ (ዶ/ር) ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ፓትሪስ ሞትሴፔ በኢትዮጵያ በሚካሄደው 46ኛው የካፍ ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ለመሳተፍ ነው አዲስ አበባ የገቡት።
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ፣…