Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጨዋታ በጁባ ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ከኤርትራ ጋር የደርሶ መልስ ጨዋታዋን በደቡብ ሱዳን ጁባ እንደምታደርግ ተገለጸ፡፡ በዚሁ መሠረት የሀገራቱ የደርሶ መልስ ጨዋታዎች ጥቅምት 21 ቀን 2017 እና ጥቅምት 24 ቀን 2017 እንደሚከናወኑ መገለጹን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡
Read More...

መሳይ ተፈሪ የዋሊያዎቹ ጊዜያዊ አሰልጣኝ ሆኑ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ገብረ መድኅን ኃይሌን በመተካት መሳይ ተፈሪ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋሊያዎቹ) ጊዜያዊ ዋና አሰልጣኝ ሆኑ፡፡ በዚሁ መሠረት አሰልጣኝ መሳይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) ማጣሪያ የሚያደርጋቸውን ጨዋታዎች እንዲመሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስኗል፡፡ አሰልጣኙ…

የ3ኛ ሳምንት የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሦስተኛ ሳምንት ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥሉ ባርሴሎና እና ባየርን ሙኒክ የሚያደርጉት ፍልሚያ አጓጊ ሆኗል፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ቤርጋሞ ላይ የጣሊያኑ አታላንታ ከስኮትላንዱ ሴልቲክ እንዲሁም የፈረንሳዩ ብረስት ከጀርመኑ ባየር ሌቨርኩሰን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር…

የካፍ ጉባዔ በኢትዮጵያ መካሄዱ ለእግር ኳሱ መነቃቃት ይፈጥራል – ም/ጠ/ሚ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 46ኛው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢትዮጵያ መካሄዱ ለሀገራችን እግር ኳስ መነቃቃት ይፈጥራል ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡ 46ኛው የካፍ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ዛሬ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። አቶ ተመስገን በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት…

የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲደረጉ ሪያል ማድሪድ ከቦሩሲያ ዶርትሙንድ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡ ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ ኤሲሚላን ከቤልጂየሙ ክለብ ብሩዥ እንዲሁም የፈረንሳዩ ሞናኮ ከሰርቢያው ሬድ ስታር ቤልግሬድ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 4…

የካፍ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል። በስብስባው ላይ የካፍ ፕሬዚዳንት እና የኮሚቴው ሰብሳቢ ፓትሪስ ሞትሴፔን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ጅራ እንዲሁም ጨምሮ ሌሎች የኮሚቴው አባላት ተገኝተዋል፡፡ በተመሳሳይ የሴካፋ አባል…

በቶሮንቶ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 11፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ ቶሮንቶ በተካሄደ የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታ አሸንፈዋል፡፡ አትሌት ዋጋነሽ መካሻ በቶሮንቶ ሴቶች ማራቶን ርቀቱን 2 ሰዓት 20 ደቂቃ ከ44 ሰከንድ በማጠናቀቅ ቀዳሚ ሆናለች፡፡ በተመሳሳይ በወንዶች ቶሮንቶ ማራቶን ውድድር አትሌት ሙሉጌታ አሰፋ አሸንፏል፡፡…