Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ማንቼስተር ዩናይትድ ከቶተንሃም የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የዛሬ መርሐ-ግርብ ሲቀጥል ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ፡፡ በዚሁ መሠረት 10 ሠዓት ላይ ኢፕስዊች ታውን በሜዳው አስቶን ቪላን የሚያስተናግድ ሲሆን÷ አስቶንቪላ የማሸነፍ ዕድሉ ከፍተኛ መሆኑ በቅድመ-ጨዋታ ግምት እየተገለጸ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል በዛሬው የመጨረሻ ጨዋታ መርሐ-ግብር 12 ሠዓት ከ30 ላይ በኦልድ ትራፎርድ የሚደረገው የማንቼስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡ ምንም እንኳን ቀያይ ሰይጣኖቹ እንደሚያሸንፉ ቢገለጽም ከቶተንሃም…
Read More...

አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አርሰናል እና ቼልሲ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል፡፡ በኢሜሬትስ ሌስተር ሲቲን ያስተናገደው አርሰናል 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸነፏል፡፡ ለአርሰናል ሊያንድሮ ትሮሳርድ(ሁለት) እና ጋብሬል ማርቲኔሊ እና ካይ ሀቨርትዝ ሲያስቆጥሩ የሌስተር ሲቲን ሁለት ጎሎች ጄምስ ጀስቲን አስቆጥሯል፡፡…

ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል ዩናይትድ ነጥብ ተጋሩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ6ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ሲቲ እና ኒውካስል አቻ ተለያይተዋል፡፡ ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ በተደረገው ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በዮስኮ ጋቫርዲዮል ጎል ቀዳሚ መሆን ቢችልም ከእረፍት መልስ አንቶኒ ጎርደን ፍፁም ቅጣት ምቱን ወደ ጎል ቀይሮ ባለሜዳዎቹን አቻ አድርጓል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር…

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ስድስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ ይካሄዳሉ። ቀን 8 ሰዓት ከ30 ላይ ኒውካስል ዩናይትድ የሊጉን መሪ ማንቼስተር ሲቲን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል። እንዲሁም ቀን 11 ሰዓት ላይ አርሰናል ሌስተር ሲቲን፣ ብሬንትፎርድ ዌስትሃም ዩናይትድን፣ ቼልሲ ብራይተንን፣ ኤቨርተን ክሪስታል ፓላስን…

ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 2 ለ1 አሸንፏል፡፡ 10 ሰዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን የማሸነፊያ ግቦች ፍፁም ጥላሁንና አማኑኤል ኤርቦ አስቆጥረዋል፡፡ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን ከሽንፈት ያልታደገችዋን ብቸኛ ግብ…

የሲቲው አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ከውድድር ዓመቱ ተሳትፎ ውጪ ሆነ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ስፔናዊው የማንቼስተር ሲቲ አማካይ ሮድሪጎ ሄርናንዴዝ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት ከ2024/25 የውድድር ዓመት ተሳትፎ ውጪ መሆኑን ክለቡ አስታውቋል፡ ተጫዋቹ ጉዳቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ከአርሰናል ጋር ባደረገው የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ላይ ነበር፡፡ የ28 ዓመቱ የዩሮ 2024 አሸናፊ ሮድሪ…

በፕሪሚየር ሊጉ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የሁለተኛ ሳምንት ጨዋታ ስሑል ሽረ እና ሐዋሳ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል። ስሑል ሽረ ፋሲል አስማማው በ48ኛው ደቂቃ ባስቆጠራት ጎል ሲመራ ቢቆይም÷ የስሑል ሽረው መሐመድ ሱሌይማን በ93ኛው ደቂቃ በራሱ ላይ ባስቆጠራት ግብ ሐዋሳ ከተማ ነጥብ እንዲጋራ አስችሎታል፡፡ በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ…