ስፓርት
በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሐዋሳ ከተማን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በድሬዳዋ ስታዲየም በተደረገው 3ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ-ግብር ኢትዮጵያ ቡና ሐዋሳ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ::
የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች ኮንኮኒ ሀፍዝ፣ ረምኬል ጀምስ እና ዳዊት ሽፈራው ሲያስቆጥሩ÷ ለየዋሳ ከተማን ብቸኛ ግብ አሊ ሱሌማን ከመረብ አሳርፏል፡፡
እንዲሁም መቻል ወላይታ ድቻን 3 ለ 1 በአሸነፈበት ጨዋታ÷ ምንይሉ ወንድሙ፣ ሽመልስ በቀለ እና በረከት ደስታ ለመቻል፤ ቴዎድሮስ ታፈሰ ደግሞ ለድቻ ጎሎቹን አስቆጥረዋል፡፡
Read More...
የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሰልጠኝ አሊዩ ሲሴን አሰናበተ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት አመታት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አሰልጠኝ የነበረው አሊዩ ሲሴ መሰናበቱ ተነገረ።
የሴኔጋል እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአስልጣኙ ኮንትራት በማለቁ ማሰነበቱን በመግለጽ አሰልጣኙ በብሔራዊ ቡድኑ ጋር ለነበረው ስኬት አመስግኗል፡፡
የ48 ዓመቱ አሊዩ ሲሴ በአሰልጣኝነት ከሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ጋር የአፍሪካ ዋንጫን ያነሳ…
2ኛ ዙር የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ይደረጋሉ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 22፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ 2ኛ ዙር የሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ቀጥለው ሲደረጉ የእንግሊዙ አስቶንቪላ ከረጅም ዓመታት ቆይታ በኋላ ባየርን ሙኒክን ይገጥማል፡፡
ምሽት 1 ሰዓት ከ45 ላይ የስፔኑ ዢሮና ከኔዘርላንድሱ ፌይኑርድ እንዲሁም ሻካታር ዶኔስክ ከአትላንታ ይጫወታሉ፡፡
በሌላ ጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 4 ሰዓት…
በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽረ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽረ አቻ ተለያይተዋል፡፡
ፋሲል ከነማ እና ስሑል ሽረ 10 ሠዓት ላይ በድሬዳዋ ስታዲየም ጨዋታቸውን አድርገው 0 ለ 0 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡
የዕለቱ የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ባህርዳር ከተማ እና…
በሻምፒየንስ ሊጉ አርሰናል ከፒኤስጂ የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር ጨዋታዎች ዛሬ ሲደረጉ አርሰናል በሜዳው ከፈረንሳዩ ፒኢስጂ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
እንዲሁም ምሽት 1 ሠዓት ከ45 ላይ በሬድ ቡል አሬና የኦስትሪያው ሬድ ቡል ሳልዝበርግ ከፈረንሳዩ ብረስት እንዲሁም የጀርመኑ ስቱትጋርት ከቼክ ሪፐብሊኩ ስፓርታ ፕራግ ይጫወታሉ፡፡
በሌላ…
ሳሙኤል ኤቶ በፊፋ ቅጣት ተላለፈበት
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማህበር (ፊፋ) ዲሲፕሊን ኮሚቴ በካሜሩን እግር ኳስ ማህበር ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ኤቶ ላይ ቅጣት መጣሉን አስታውቋል፡፡
የቀደሞ የባርሴሎና እና ኢንተርሚላን ኮከብ ቅጣት የተላለፈበት ያልተገባ ባህሪ በማሳየቱ እና የፊፋን ፍትሃዊ የጨዋታ መርሆች በመጣሱ ነው ተብሏል፡፡
ኤቶ ድርጊቱን የፈጸመው…
መቐለ 70 እንደርታ ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በ3ኛ ሳምንት ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መቐለ 70 እንደርታ ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተደረገው ጨዋታ ያሬድ ብርሃኑ የመቐለ 70 እንደርታን ብቸኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡
የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል ምሽት 1 ሰዓት ላይ ኢትዮጵያ መድህን እና አዲስ አዳጊው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጨዋታቸውን…