Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

ሀገሩን በኦሊምፒክ የመወከል ህልም ያለው የጅምናስቲክ ተወዳዳሪ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጅምናስቲክ ስፖርት ተወዳዳሪው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ድሪባ ቶሌራ በኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ስኬታማ ጊዜን እያሳለፈ ይገኛል፡፡ በስፖርት ፌስቲቫሉ በትናንትናው ዕለት ፍፃሜውን ባገኘው የጅምናስቲክ ውድድር አስተናጋጁ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በ76 ነጥብ 1ኛ በመሆን የቡድን ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል:: የዩኒቨርሲቲው የሲቪል ምህንድስና 2ኛ ዓመት ተማሪ የሆነው ድሪባ ቶሌራ በተወዳደራባቸው የጅምናስቲክ የስፖርት አይነቶች አራት የወርቅና አንድ የብር ሜዳልያዎችን…
Read More...

በኖርዊች ሲቲ ድንቅ ብቃቱን እያስመለከተ የሚገኘው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሊ አህመድ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከካናዳው ቫንኩቨር ኋይትካፕ የእንግሊዙን ኖርዊች ሲቲ በጥር የዝውውር መስኮት የተቀላቀለው ትውልደ ኢትዮጵያዊው አሊ አህመድ በርካቶችን በብቃቱ እያስደመመ ይገኛል፡፡ አሊ አህመድ በፈረንጆቹ 2000 በካናዳ ቶሮንቶ የተወለደ ሲሆን ወላጆቹ ከ30 ዓመታት በፊት ከሐረርጌ ወደ ካናዳ በማቅናት ኑሯቸውን በዚያው አድርገዋል።…

ቼልሲ እና ራሂም ስተርሊንግ በስምምነት ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) እንግሊዛዊው የክንፍ ተጫዋች ራሂም ስተርሊንግ ከቼልሲ ጋር በስምምነት ተለያይቷል፡፡ በቼልሲ ቤት 325 ሺህ ሳምንታዊ ደመወዝ ያገኝ የነበረው የ31 ዓመቱ ተጫዋች ስተርሊንግ፤ ቀሪ የ18 ወራት የኮንትራት ውል ነበረው። ስተርሊን በ2022 ከማንቼስተር ሲቲ በ47 ነጥብ 5 ሚሊየን ፓውንድ የምዕራብ ለንደኑን ክለብ መቀላቀሉ…

ሉካስ ፓኩኤታ ፍላሚንጎን ለመቀላቀል ከስምምነት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብራዝላዊው የፊት መስመር ተጫዋች ሉካስ ፓኩኤታ የሃገሩን ክለብ ፍላሚንጎን በ41 ሚሊዮን ዩሮ ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል፡፡ የ28 አመቱ ተጫዋች በ2022 ከፈረንሳዩ ሊዮን ዌስትሃም ዩናይትድን መቀላቀሉ ይታወሳል፡፡ ሉካስ ፓኩኤታ በክለቡ እንዲቆይ ግፊት ብናደርግም በተጫዋቹ የቤተሰብ እና ሌሎች ጉዳዮች መልቀቂያውን…

7ኛው የመላ አፋር ስፖርት ውድድር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 7ኛው የመላ አፋር ስፖርት ውድድር “አንድነት ለጥንካሬያችን ስፖርት ለሠላማችን” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው፡፡ በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የክልሉ ማህበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪና የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ ሐሚድ ዱላ እንዳሉት÷ ውድድሩ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ስፖርተኞችን ማፍራት ያስችላል፡፡…

በማንቼስተር ሲቲ አጀማመሩ የሰመረለት አንቶኒዮ ሴሜንዮ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፕሪሚየር ሊጉ በቦርንማውዝ በመድመቅ ደረጃውን ከፍ አድርጎ ወደ ኢትሃድ ያቀናው አንቶኒዮ ሴሜንዮ በማንቼስተር ሲቲ ቤት በፍጥነት መላመድ ችሏል፡፡ ከጋናዊ አባቱ እና ፈረንሳዊ እናቱ በፈረንጆቹ 2000 በእንግሊዝ የተወለደው ሴሜንዮ በሊጉ ደማቅ አንቅስቃሴን እያደረጉ ከሚገኙ የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡…

ከ2010 የዓለም ዋንጫ በኋላ ምርጥ ብቃቱ የከዳው ቶሬስ…

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የዓለም እግር ኳስ ከተመለከታቸው ምርጥ የፊት መስመር ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነው የስፔን ብሔራዊ ቡድን የቀድሞ ኮከብ ፈርናንዶ ቶሬስ፡፡ ቶሬስ በተጫዋችነት ዘመኑ ከምርጥ አጥቂዎች መካከል አንዱ የነበረ ሲሆን÷ በፍጥነቱ፣ በጎል አስቆጣሪነቱ እና በድንቅ ችሎታው ይታወቃል፡፡ ፈርናንዶ ቶሬስ ለተከላካዮች ፈታኝ ከመሆኑ ባለፈ…