ስፓርት
አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወትና አትሌት ቢቂሌ አንበሴ የ10 ኪ.ሜ የጐዳና ውድድርን አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት እና አትሌት ቢቂሌ አንበሴ የ1ኛው የኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ውድድርን አሸንፈዋል።
ዛሬ ማለዳ በሐዋሳ ከተማ በተደረገው የ10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ውድድር በወንዶች አትሌት ሀጎስ ገ/ህይወት በቀዳሚነት አጠናቅቋል።
አትሌት ሀጎስ ውድድሩን ለማጠናቀቅ 28 ደቂቃ 2 ሰከንድ ከ94 ማይክሮ ሰከንድ ፈጅቶበታል።
አትሌት ገመቹ ዲዳ ሁለተኛ እንዲሁም አትሌት አሊ ቃሲም ሶስተኛ በመሆን ውድድሩን ጨርሰዋል፡፡
በሴቶች ምድብ በተደረገ የ 10 ኪሎ ሜትር የጐዳና ላይ…
Read More...
አርሰናል ከማንቼስተር ዩናይትድ የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) 23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ ቀጥሎ ሲካሄድ የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በኢምሬትስ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር የሚያደርጉት ፍልሚያ በጉጉት ይጠበቃል፡፡
በሊጉ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ማሸነፍ ያልቻለው የሚኬል አርቴታ ቡድን አርሰናል ወደ አሸናፊነት ለመመለስና መሪነቱን ለማጠናከር…
ማንቼስተር ሲቲ ወልቭስን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ወልቭስን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
የማንቼስተር ሲቲን ግቦች ኦማር ማርሙሽ እና አንቶኒዮ ሴሜኒዮ አስቆጥረዋል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ ነጥቡን ወደ 46 ከፍ በማድረግ የሊጉ መሪ አርሰናል ነገ ጨዋታውን እስከሚያደርግ ያለውን የነጥብ…
አርሰናል ከማንቼስተር ዩናይትድ – ተጠባቂው ፍልሚያ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ23ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ዛሬ በሚደረጉ አምስት ጨዋታዎች ይጀምራል፡፡
ምሽት 12 ሰዓት ላይ ማንቼስተር ሲቲ በሜዳው ኢትሃድ በውድድር ዓመቱ እስካሁን አንድ ጨዋታ ብቻ ካሸነፈው ወልቭስ ጋር ይጫወታል፡፡
በሊጉ ካደረጋቸው ያለፉት አራት ጨዋታዎች በአንዱም ማሸነፍ ያልቻለው ማንቼስተር ሲቲ ወደ ድል…
ማንቼስተር ዩናይትድ ለኮቢ ማይኑ አዲስ ውል ለማቅረብ ዝግጁ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ማንቼስተር ዩናይትድ ወጣቱን አማካይ ኮቢ ማይኑ ለረዥም ዓመታት በክለቡ ለማቆየት አዲስ ውል የማቅረብ ፍላጎት እንዳለው ተነግሯል፡፡
የ20 ዓመቱ እንግሊዛዊ በፈረንጆቹ 2023 ከማንቼስተር ዩናይትድ አካዳሚ ወደ ዋናው ቡድን ካደገ ወዲህ ለክለቡ ባደረጋቸው 87 ጨዋታዎች ሰባት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ተጫዋቹ በተለይም…
ካሴሚሮ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር ይለያያል
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የ33 ዓመቱ ብራዚላዊ አማካይ ካሴሚሮ በውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከማንቼስተር ዩናይትድ ጋር እንደሚለያይ ተነግሯል።
ተጫዋቹ በዩናይትድ የሚያቆየው ውል በመጪው ክረምት ሲጠናቀቅ ለተጨማሪ አንድ አመት ቆይታውን የማራዘም አማራጭ ቢኖርም ክለቡ ውሉን ለማራዘም ፍላጎት እንደሌለው ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ይህን ተከትሎ…
ሲዳማ ቡና እና መቻል አሸነፉ
አዲስ አበባ፣ ጥር 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ16ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር የሊጉ መሪ ሲዳማ ቡና ኢትዮጵያ ቡናን 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 10 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግቦች ብለስ ናጎ ፣ ዮሴፍ ዮሀንስና ፍራኦል መንግሥቱ አስቆጥረዋል።
በሌላ በኩል መቻል ቅዱስ ጊዮርጊስን 2 ለ 0…