Fana: At a Speed of Life!

ስፓርት

አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ከባየር ሊቨርኩሰን ተሰናበቱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የጀርመኑ ክለብ ባየር ሊቨርኩሰን አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግን አሰናብቷል፡፡ አሰልጣኙ ከማንቼስተር ዩናይትድ ከተሰናበቱ በኋላ ያለ ክለብ የቆዩ ሲሆን፥ በዚህ ክረምት ስፔናዊውን ዣቢ አሎንሶ ተክተው ባየር ሊቨርኩሰንን መረከባቸው ይታወሳል፡፡ ሊቨርኩሰን በቡንደስሊጋው ባደረጋቸው ሁለት ጨዋታዎች በአንዱ ተሸንፎ በአንዱ አቻ የተለያየ ሲሆን፥ ማግኘት ከነበረበት ስድስት ነጥብ ማሳካት የቻለው አንዱን ብቻ ነው፡፡ የክለቡ አመራሮች ባለፉት ሳምንታት የቡድኑን እንቅስቃሴ በመገምገም አሰልጣኙን…
Read More...

በዛሬው ዕለት የተደረጉ ዝውውሮች…

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 26፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን በርካታ ተጫዋቾች ወደተለያዩ ክለቦች በመዘዋወር ላይ ይገኛሉ፡፡ ሊቨርፑል የክለቡ ክበረወሰን በሆነ 130 ሚሊየን ፓውንድ የዝውውር ሂሳብ አሊክሳንደር ኢሳክን ከኒውካስል ዩናይትድ ለማስፈረም ተስማምቷል፡፡ ተጫዋቹ በዛሬው ዕለት የህክምና ምርመራውን…

በሜክስኮ ማራቶን አትሌት ታዱ አባተ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሜክሲኮ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ታዱ አባተ አሸንፏል፡፡ አትሌቱ  ርቀቱን  2 ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ15 ሰከንድ በመጨረስ ነው ውድድሩን በቀዳሚነት ያጠናቀቀው፡፡ በርቀቱ የተሳተፈው ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዳነ ከበደ 2 ሰዓት ከ13 ደቂቃ ከ54 ሰከንድ በመግባት አራተኛ ደረጃን ይዟል፡፡

ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን ተሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ3ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ በብራይተን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ተሸንፏል፡፡ የብራይተንን የማሸነፊያ ግቦች ጀምስ ሚልነር በፍፁም ቅጣት ምት እና ግሩዳ ሲያስቆጥሩ የማንቼስተር ሲቲን ብቸኛ ግብ ኤርሊንግ ብራውት ሀላንድ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ውጤቱን ተከትሎ ማንቼስተር ሲቲ በሊጉ ተከታታይ…

አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ በሲድኒ የማራቶን ውድድር አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 25፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሲድኒ የወንዶች ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ አሸንፏል። በዓለም አትሌቲክስ ሜጀር ማራቶን ውስጥ በተካተተው 2025 የሲድኒ ማራቶን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸናፊ ሆነዋል። በዚህም በወንዶች አትሌት ኃይለማርያም ኪሮስ 2 ሰዓት ከ06 ደቂቃ ከ06 ሰከንድ በመግባት ውድድሩን በቀዳሚነት አጠናቋል።…

ሞሮኮ የቻን ዋንጫን ለ3ኛ ጊዜ አነሳች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በስምንተኛው የአፍሪካ ሀገራት ሻምፒዮና (ቻን) የፍጻሜ ጨዋታ ሞሮኮ ማዳጋስካርን 3 ለ 2 አሸንፋለች። ዛሬ ማምሻውን በካሳራኒ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኡሳማ ላምላዊ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር የሱፍ ሜህሪ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል። ክላቪን ፌሊሲት ማኖሃንቶሳ እና ቶኪ ኒአና ራኮቶንድራይቤ ደግሞ…

ቼልሲ አሌሃንድሮ ጋርናቾን አስፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቼልሲ አርጀንቲናዊውን የክንፍ መስመር አጥቂ አሌሃንድሮ ጋርናቾን ከማንቼስተር ዩናይትድ ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ጋርናቾ በሰባት ዓመት ውል በ40 ሚሊየን ፓውንድ ሒሳብ ነው ለምዕራብ ለንደኑ ክለብ ፊርማውን ያኖረው፡፡ አርጀንቲናዊው ወጣት ተጫዋች በማንቼስተር ዩናይትድ ትልቅ ተስፋ…