Fana: At a Speed of Life!

ጉምሩክ ኮሚሽንና የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለመከላከያ ሰራዊት ያዘጋጁትን ድጋፍ አስረከቡ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን እንዲሁም የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ለሀገር መከላከያ ሰራዊት እንዲሆን ያዘጋጁትን ድጋፍ አስረክበዋል፡፡
የጉምሩክ ኮሚሽን የ602 ሺህ ብር ግምት ያለው የአይነት እና አንድ ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ደግሞ 50 ፍየሎች ድጋፍ አድርገዋል።
ድጋፉ በተለይም በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸውና በህክምና ላይ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የሚውል ነው ተብሏል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ እና የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ ተፈሪ መኮንን እንደገለጹት÷ለሃገር ሰላምና ደህንነት የሚከፈል ዋጋ አካል በመሆናችን ደስተኞች ነን፤ ዘመቻው ተጠናቆ ሃገር ሰላም እስክትሆን ድረስ ድጋፋችን ይቀጥላል፡፡
ድጋፉን የተረከቡት የጦርሃይሎች ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስልጠናና ምርምር ዳይሬክተር ኮ/ል ዶ/ር አሰማ ተፈራ÷ አሸባሪው ህወሃት በሰራዊቱ ላይ ክህደት ፈጽሞ ወደ ጦርነት ከገባንበት ጊዜ ጀምሮ ህዝቡ ያልተቋረጠ ድጋፍ በማድረግ ከጎን ተለይቶ አያውቅም ብለዋል።
በሃይማኖት ኢያሱ
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.