Fana: At a Speed of Life!

በሲዳማ ክልል በግብርና ቴክኖሎጂ ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 24፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ደስታ ሌዳሞ በክልሉ የግብርና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ አሉ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ በክልሉ በተለያዩ ወረዳዎች በመኸር አርሻ እየተከናወነ ያለውን የሰብል ልማት ተዘዋውረው በመመልከት አርሶ አደሮችን አበረታተዋል።
በዚህ ወቅትም በክልሉ በ2017/18 የመኸር እርሻ በዋና ዋና ሰብሎች 3 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በመኸር እርሻው የግብርና ቴክኖሎጂን በአግባቡ በመጠቀም የአርሶ አደሩን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ ይገኛል ነው ያሉት፡፡
አሲዳማ መሬትን ለማከም የኖራ አቅርቦትና አጠቃቀም እንዲሻሻል ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ ትኩረት በመሰጠቱ አርሶ አደሩ ኖራን በአግባቡ እንዲጠቀም ማድረግ ተችሏል።
በተጨማሪም የአርሶ አደሩ የምርጥ ዘር እና የማዳበሪያ አጠቃቀም እየተሻሻለ እንዲመጣ መደረጉን ነው ያስረዱት፡፡
በሌላ በኩል የሰብል በሽታ መከላከልና አረም ቁጥጥር ሥራ በአግባቡ እንዲመራ በትኩረት እንደሚሰራ አመልክተዋል፡፡
ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
Amharic Entertainment YouTube www.youtube.com/@fanaentertainment
Amharic Podcast YouTube www.youtube.com/@fanamcpodcast በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስለሆኑ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.