Fana: At a Speed of Life!

ጀርመን በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መሪነት በኢትዮጵያ እየተከነወነ ያለውን ለውጥ እንደምትደግፍ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር አገራቸው የኢትዮጵያ የልማት አጋር መሆኗንና በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መሪነት በአገሪቱ እየተከናወነ ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ እንደምትደግፍ አስታወቁ።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውየርን ዛሬ በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይቱ ዶክተር ፍፁም አሰፋ፥ ኢትዮጵያ እየተገበረች በምትገኘው የ10 ዓመቱ የልማት ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ለአምባሳደሩ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ኢትዮጵያ ከልማት ትብብር የምታገኘውን ድጋፍ አስመልክተው የመከሩ ሲሆን፥ ድጋፉ ለኢትዮጵያ ልማት ያለው አስተዋጽኦ ቀላል አለመሆኑንም አስረድተዋል።

በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አውየር በበኩላቸው፥ አገራቸው የኢትዮጵያ የልማት አጋር መሆኗን ጠቅሰው፣ መንግስታቸው ኢትዮጵያ እያከናወነች ያለውን የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ለውጥ እንደሚደግፍ ገልጸዋል።

በተጨማሪም የጀርመን መንግስት የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አመራርን እንደሚደግፍ በመግለጽ፣ ወደፊትም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ተባብሮ ለመስራት ቁርጠኛ መሆኑን ጨምረው አመልክተዋል።

የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር መባደረጉት በዚህ ውይይት በቀጣይ ኢትዮጵያ እና ጀርመን በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎችና በልማት ፕሮግራሞች ትብብራቸውን ለማጠናከር መስማማታቸውን ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.