Fana: At a Speed of Life!

አቶ ወርቁ አይተነው ለመከላከያ ሰራዊት 50 ሰንጋዎችን አበርክቱ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ቀጠና ተሰማርቶ ግዳጁን በመፈፀም ላይ ለሚገኘው ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት 50 ሰንጋዎችን በስጦታ አበርክተዋል።
በርክክብ ሥነ ሥርአቱ ወቅት አቶ ወርቁ አይተነው እንዳሉት ፣ ኢትዮጵያ ጀግኖች በምትፈልግበት ቦታ ሁሉ አኩሪ ገድል የሚፈጽሙ አኩሪ ልጆች አሏት ፡፡
 
ጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን እና የክልል ልዩ ሃይሎች አባላት በጠላት ላይ አኩሪ ጀብድ መፈጽማቸውንም አድንቀዋል ፡፡
 
በስፍራው የሚገኘው የሰራዊት ክፍል ከፍተኛ አመራር በበኩላቸው፥ ለተደረገው ድጋፍ በሰራዊቱ ስም ምስጋና አቅርበው፥ባለሀብቱ
ለሰራዊቱ ያደረጉት ድጋፍ ሀገር ወዳድነታቸውን ያሳያል፤ ድጋፉም ለሠራዊቱ የሞራል ስንቅ ይሆናል ማለታቸውን ከመከላከያ ሰራዊት የማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
 
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.