Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ ከተማ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ወደ ተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ መግባት ጀመሩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 1፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተማ አስተዳደሩ የ2016 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናውን ወደሚወስዱባቸው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መግባት ጀመሩ።

ከሐምሌ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮም የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ፣ አራት ኪሎ፣ ኤፍቢኢ እና አምስት ኪሎ ካምፓሶች ሲገቡ አበረታትተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.