ወ/ሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)ወይዘሮ ቡዜና አልቃድር የአዲስ አበባ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል።
የምክር ቤቱ አባላት ወይዘሮ ቡዜና አፈ-ጉባኤ ሆነው እንዲሾሙ በሙሉ ድምጽ ደግፈዋል።
ወይዘሮ ቡዜና ለህገ መንግስቱ ታማኝ በመሆን ስራቸውን ህግን መሰረት በማድረግ እንደሚፈጽሙ ቃል በመግባት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።
በተጨማሪም ወይዘሪት ፈይዛ መሃመድ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው ተመርጠዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!