ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተመረጡ
አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የሲዳማ ክልል መንግስት የምስረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው፡፡
በጉባዔው ወይዘሮ ፋንታዬ ከበደ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ሆነው የተመረጡ ሲሆን÷ ቃለመሃላም ፈፅመዋል፡፡
ምክትል አፈ ጉባዔ በመሆን ደግሞ አቶ ዘነበ ዘርፋ ተመርጠዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!