Fana: At a Speed of Life!

በ76ኛው የመንግስታቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ የኢትዮጵያን አቋም ለአለም ግልጽ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ተግባር አከናውኗል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ76ኛው የመንግስታቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ልዑክ የኢትዮጵያን አቋም ለአለም ግልጽ በማድረግ ረገድ ውጤታማ ተግባር ማከናወኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገለጹ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ሳምንታዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራው የኢትዮጵያ ልዑክ ከተለያዩ አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በርካታ የጎንዮሽ ውይይቶች ማካሄዱንም አውስተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገራት ላይ እየተደረገ ያለው ጣልቃ ገብነት እንዲቆም በአጽንት መጠየቃቸውና፣ አሸባሪው የህውሓት ቡድን በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰው ባለው ሰብዓዊና ቁሳዊ ቀውስ ዙሪያም ሰፊ ማብራሪያ መስጠታቸውንም አንስተዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሱዳን በፈጠረችው የድንበርና ሌሎች ተዛማች ጉዳዮች ዙሪያ እንዲሁም ኢትዮጵያውያ የቀጠናውን ሰላም እና መረጋጋት ለማስጠበቅ እያካሄደች ባለው እንቅስቃሴ ዙሪያ ገለጻ ማድረጋቸውን ነው አምባሳደር ዲና ያብራሩት።

በህዳሴ ግድቡ እና በሰሜኑ የአገሪቱ ክፍል ባለው ወቅታዊ ሁኔታ፤ እንዲሁም በኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖን ለመቋቋም እያደረገች ባለችው ጥረት በተለይም እየተገበረችው ባለው የአረንጎዴ ልማት መርሃግብር ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በተለይም ከተመድ ዋና ፀሀፊ አንቶኒ ጉተሬዝ ጋር መወያየታቸውን ጠቅሰዋል።

በሌላ በኩል ለዲፕሎማቶች በተሰጠው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና እና ቀጠናዊ ጉዮዮች በጥናታዊ ስራዎች ተደግፈው ቀርበዋል ብለዋል።

ከባህሬን የንግድ እና ኢንዱስትሪ ቻምበር ጋር ስምምነት መፈረሙንም ጠቁመዋል።

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ፥ አድሎአዊና የተዛባ መረጃ እያሰራጩ ያሉ ዓለም አቀፍ የሚዲያ ተቋማትን በሲ ኤን ኤን ዋና ማሰራጫ ማዕከል ፊት ለፊት በመገኘት በማውገዘ ሀገራዊ ሃላፊነታቸውን ለመወጣት ያደረጉትን ጥረት ጠቅሰዋል አምባሳደር ዲና።

በወንደሰን አረጋኽኝ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.