Fana: At a Speed of Life!

የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰልፍ ቅዳሜ በካናዳ ሊካሄድ ነው

አዲስ አበባ፣ ህዳር 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በካናዳ የሚኖሩ ትውልደ-ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ወጣቶች ያዘጋጁት የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የፊታችን ቅዳሜ በካናዳ መዲና ኦቶዋ እንደሚካሄድ የኢትዮ-ካናዳውያን ዩዝ ኔትወርክ ጥምረት አስታወቀ፡፡
ህዳር 11 ቀን 2014 ዓ.ም የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይ እንደሚጀመር ጥምረቱት ለኢዜአ ተናግሯል፡፡
ሰልፉ መነሻውን የኦቶዋ ከተማ አዳራሽ በማድረግ በካናዳ ፓርላማ፣ በአሜሪካ ኤምባሲና በካናዳ ብሮድካስቲንግ ሰርቪስ ፊት ፊት ይካሄዳል ነው የተባለው፡፡
በሰልፉ አንዳንድ የምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጫና የሚያወግዙ መልዕክቶች የሚተላለፉበት ሲሆን÷ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን እየሰሩ ያሉትን ግጭት አባባሽ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት እንዲያቆሙ ጥሪ እንደሚቀርብም ነው የተገለጸው።
ለካናዳ ፓርላማ እና በኦቶዋ ለሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አንዳንድ ምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና እንዲያቆሙና እጃቸውን እንዲያነሱ የሚያስገነዝብ ደብዳቤ እንደሚሰጥም ተገልጿል።
ሰላማዊ ሰልፉ እሁድ ህዳር 12 ቀን 2014 ዓ.ም የምዕራባውያን አገራት በኢትዮጵያ ላይ የሚያደርጉትን ጫና በመቃወም በመላው አለም በሚገኙ ዋና ዋና ከተሞች የሚከናወነው ሰልፍ አካል ነው።
በተጨማሪም በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የኢትዮጵያን አቋም የሚያስረዱ የዲፕሎማሲ ስራዎችን እያከናወኑ እንደሚገኙ የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ ገልጿል።
የዳያስፖራው ማህበረሰብ ህዳር 4 ቀን 2014 ዓ.ም በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ የካናዳ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ሜላኒ ጆሊ፣ ከካናዳ የቤቶች፣ የብዝሃነትና አካታችነት ሚኒስትር አህመድ ሁሴንና ከካናዳ ፓርላማ አባላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት ማድረጉንም አመልክቷል።
ውይይቱ የካናዳ መንግስት ባለስልጣናት የኢትዮጵያን አቋም ከማስረዳት አንጻር ፍሬያማ እንደነበርና በቀጣይ መሰል ውይይቶች ለማድረግ ከመግባባት ላይ መደረሱን ጠቅሷል።
የኢትዮ-ካናዳውያን ኔትወርክ ለማህበራዊ ድጋፍ በቀጣይ ከካናዳ ባለስልጣናት ጋር በወቅታዊ ሁኔታ ላይ ምክክር የሚደረግበት መድረክ እንደሚያዘጋጅም በመግለጫው አስታውቋል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.