የባሶ ሊበን ወረዳ አርሶ አደሮች በህወሓት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምሥራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ አርሶ አደሮች በአሸባሪው ቡድን ሰብላቸው የወደመባቸውን ወገኖች ለመርዳት ቃል ገብተዋል፡፡
በምሥራቅ ጎጃም ዞን በስንዴ ምርታቸው ከሚታወቁ ወረዳዎች መካከል አንዷ የሆነችው የባሶ ሊበን ወረዳ በሰብል ስብሰባ ላይ ትገኛለች።
አርሶ አደሮችም ሰብላቸውን በኮምባይነር እየሰበሰቡ ሲሆን ይህም በምርት ላይ ይደርስ የነበረውን ብክነት ከመቀነስ ባለፈ ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘባቸውን እንደቆጠበላቸው አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
አርሶ አደሮቹ ያገኙት ምርት ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር የተሻለ መሆኑን ገልጸው ያገኙትን ምርት በአሸባሪ ቡድን የበቀል እጅ አርፎባቸው ከቤት ንብረታቸው ከተፈናቀሉ ዜጎች ጋር እኩል ተካፍለው ለመብላት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
በወረራው የታጣውን ምርት ለማካካስ ተጨማሪ ምርት እንደሚያመርቱም ገልጸዋል።
በባሶ ሊበን ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ቤት የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ስሜነህ አሞኜ ካለው ወቅታዊ አገራዊና ክልላዊ ሁኔታ አንፃር የተገኘውን ምርት በአጭር ጊዜ ለመሰብሰብ እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ግብርና መምሪያ ምክትል ሃላፊ አቶ አበበ ጓዱ በበኩላቸው በዞኑ ከ24 በላይ የምርት መሰብሰቢያ ኮምባይነሮች ገብተው የአርሶ አደሩን ሰብል እየሰበሰቡ መሆኑን ተናግረዋል።
አሸባሪውና ወራሪው ኀይል በግብርና ሥራው ላይ ያደረሰውን ውድመት ለማካካስና የተጎዱና የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ ታሳቢ አድርገው እየሠሩ መሆኑን አሚኮ ዘግቧል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!