የሴቶች መብት ሊከበር የሚችለዉ የይስሙላ ያልሆኑ እርምጃዎች ሲወሰዱ ነው- ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 16፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የሴቶችን መብት ከመፈክር አዉርደን ተግባራዊ የሚሆንበትን መሰላል ማዘጋጀት አለብን ሲሉ ፕሬዚደንት ሳህለወርቅ ዘዉዴ ገለጹ፡፡
ፕሬዚደንቷ የፀረ-ፆታ ጥቃት ቀንን አስመልክተዉ ባደረጉት ንግግር÷ የሴቶችን መብት ለማስከበር የ365 ቀንና የ24 ሰዓት ስራችን መሆን አለበት ብለዋል፡፡
ባለፉት ዘመናት ያልተፈቱ ችግሮች በ21ኛው ክፍለ ዘመን እየተስተዋሉ መሆኑን ያመላከቱት ፕሬዚደንቷ÷ የሴቶች እኩልነት፣ መብትና ደህንነት ሊከበር የሚችለዉ የይስሙላ ያልሆኑ እርምጃዎች ሲወሰዱ ነው ማለታቸውን ከማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በበኩላቸዉ÷ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ አጽዕኖት ሰጥቶ ለማስገንዘብ ያለሙ የንቅናቄ ስራዎች እንዲካሄዱ በቅንጅት እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!