Fana: At a Speed of Life!

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን 35 ሺህ 344 ሄክታር መሬት በዘር ተሸፍኗል- የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ

 

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል በሽብርተኛው ህወሓት ቡድን የወደሙ ሰብሎችን ለማካካስ በዳግም ልማትና በቅብብሎሽ ምርት ለማምረት እየተሰራ መሆኑን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ገለፀ፡፡

በመስኖ ልማት፣ በቀሪ እርጥበት ወይም በዳግም ልማትና በቅብብሎሽ ሰብል ለማምረት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እየተፈፀመ ይገኛልም ነው የተባለው፡፡

በዚህም በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምዕራብና ምስራቅ ደምቢያ ወረዳዎች በዳግም ልማትና በቅብብሎሽ ሰብል ለማምረት በስፋት እየተሰራ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ÷የሚባክን ውሃ፤ ጉልበትና አቅም እንደሌለ እነዚህ ወረዳዎች በተግባር አሳይተዋል ተብሏል፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በዳግም ልማት ( በቀሪ እርጥበት ) 35 ሺህ 344 ሄክታር እንዲሁም በቅብብሎሽ 12 ሺህ 442 ሄክታር መሬት በዘር መሸፈኑን ከክልሉ ግብርና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ግብርና ቢሮ የቴክኒክ ቡድን በዞኑ እየተከናወነ ያለውን የግብርና ልማት ስራ ውጤታማ እንዲሆን ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ለአርሶ አደሩ ድጋፉን ተደራሽ መደረጉን የጠቆመው ቢሮው ድጋፉም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጿል፡፡

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.