“ሀገርን ለማፍረስ እስከ ሲኦል እሄዳለሁ”ያለውን ቡድን በቅርቡ ወደ ተመኘው ሲኦል እንሸኘዋለን”- ኮ/ል ገዛኸኝ ነጋሽ
አዲስ አበባ፣ ህዳር 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሀገርን ለማፍረስ እስከ ሲኦል እሄዳለሁ” ያለውን አሸባሪ ቡድን በቅርቡ ወደ ተመኘው ሲኦል እንሸኘዋለን አሉ የኢትዮጵያ አየር ኃይል አካዳሚ አዛዥ ኮሎኔል ገዛኸኝ ነጋሽ ።
አካዳሚው በአውሮፕላን ሞተር ጥገናና በኤሌክትሮኒክስ ሙያ በደረጃ ያሰለጠናቸውን የአቪዬሽን ሙያተኞችን አስመርቋል።
በመርሃ ግብር ላይ የተገኙት የአካዳሚው አዛዥ ኮሎኔል ገዛኸኝ ነጋሽ እንዳሉት÷ ያለንበት ወቅት በተመረቅንበት ሙያ ብቻ ህዝብና ሀገርን የምናገለግልበት ጊዜ ሳይሆን ድርብ ኃላፊነትን በመውሰድ አኩሪ ገድል የምንፅፍበት ወቅት ነው።
የጥፋት ቡድኑ ከውስጥና ከውጭ ታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር ተባብሮ ሀገር ለማፍረስ እየሰራ ቢሆንም እኩይ ሴራውን ለማክሸፍ ኢትዮጵያዊያን በጋራ በመረባረብ ድባቅ እየመቱት እንደሚገኙ ገልጸዋል።
ሰልጣኝ ተመራቂ የአቪዬሽን ሙያተኞች ተቋሙን በከፍተኛ ወኔና የሙያ ፍቅር ለማገልገል መዘጋጀት እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
ከተመራቂ ሰልጣኞች አንዳንዶች በሰጡት አስተያየት ፣ የዘመኑ አቪዬሽን ቴክኖሎጂ ሳይንስ የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት መቅሰማቸውን ጠቅሰው ወደፊትም ለተቋሙ የለውጥ ጉዞ ስኬታማነት የበኩላቸውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል።
የኢፌዴሪ አየር ኃይል አካዳሚ በሀገሪቱ ውስጥ አንጋፋው የአቪዬሽን አካዳሚ ሲሆን ፣ አካዳሚው በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች የመለመላቸውን የሰራዊት አባላት በአጭርና በረጅም ኮርስ በልዩ ልዩ የአቭዬሽን የሙያ ዘርፎች እያሰለጠነ እንደሚገኝ ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!