Fana: At a Speed of Life!

የቁም እንስሳት ግብይት ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ፖሊሲ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቁም እንስሳት ግብይት ላይ የሚስተዋሉ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል ፖሊሲ መዘጋጀቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ በቁም እንስሳት ግብይትና ወጪ ንግድ ላይ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ላይ ግብርና ሚኒስቴር፣ አደጋ ስጋትና ሥራ አመራር ኮሚሽን፣ ጉምሩክ ኮሚሽን፣ ቁም እንስሳት ላኪዎች ማህበርና ሌሎች ባለድርሻ ተቋማት ተሳትፈዋል ተብሏል።
ህገ ወጥ ንግድ፣ የጥራት ጉድለት፣ የእርድ እንሳስት ትራንፖርት፣ የፋይናንስ እና የእንስሳት ማቆያ ማዕከላት እጥረት በዘርፉ ከሚስተዋሉ ችግሮች መካከል ተጠቅሰዋል፡፡
ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ ከተቀባይ ሀገራት ጋር ስምምነት አለመግባቷ በዘርፉ ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑን አንስተዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ዳንጌ ቦሩ፥ በዘርፉ ባሉ ህጎች ላይ የሚታየው የአተገባበር ጉድለት ችግሮችን በሚፈለገው ደረጃ እንዳይቀረፉ እክል ፈጥሯል ብለዋል፡፡
ከዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ስለመሆኑ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የቁም እንስሳት ቆዳና ሌጦ ገበያ ጥናት ማስፋፊያ ዳይሬክተር አቶ ዴስነት በላይ ተናግረዋል ፡፡
ለገቢው መቀነስ ዘርፈ ብዙ ምክንያቶች መኖራቸውን ጠቅሰው÷ ገበያ ተኮር የእንስሳት እርባታ አለመኖሩ ደግሞ ዋነኛው ነው ብለዋል፡፡
የቁም እንስሳት መሸጫ ዋጋ ለረጅም ጊዜ ሳይከለስ መቆየቱን እና ከዚህ አኳያ የቁም እንስሳት ዝቅተኛ መሸጫ ዋጋ መመሪያ መዘጋጀቱን አክለዋል።
ዘርፉ ሁሉን አቀፍ ፖሊሲ እንዳልነበረው የተገለጸ ሲሆን÷ አሁን ላይ ችግሩን መቅረፍ የሚያስችል ፖሊሲ ተዘጋጅቶ መጠናቀቁን ኢዜአ ዘግቧል።
ፖሊሲው በቅርቡ ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
0
People reached
41
Engagements
Boost post
40
1 Share
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.