በአሸባሪው ሸኔ ምክንያት በኦሮሚያ ክልል ከ325 ሺህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል
በላይ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል 163 ትምህርት ቤቶች በሸኔ ታጣቂዎች መቃጠላቸውን እና 756 ትምህርት ቤቶች መዘረፋቸውን የኦሮሚያ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ገለፁ።
የቢሮው ሃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ እንደገለፁት፥ በአሸባሪው ሸኔ ምክንያት ትምህርት ቤቶች ላይ በደረሰው ውድመት 325 ሺህበላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ሆነዋል።
ምንም እንኳን አሸባሪው ሸኔ ኢ-ሠብዓዊ በሆነ መንገድ በትምህርት ተቋማት ላይ ውድመቶችን ቢፈጽምም፥ በክልሉ በኢፋቦሩ ፕሮጀክት ባለፈው አንድ ዓመት ከ100 በላይ ትምህርት ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 93 የሚሆኑት ከ2 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ተገንብተው የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸውን ሀላፊው ተናግረዋል።
በክልሉ ሰባት አዳሪ ትምህርት ቤቶችም መገንባታቸውን ነው ያመለከቱት፡፡