Fana: At a Speed of Life!

የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ስራ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ ስራ የጀመረው የእንጦጦ ፖርክ የመኪና ማቆሚያ የግንባታ ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ክፍት መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ፡፡
ይህ ኘሮጀክት በአጠቃላይ ሦስት የመኪና ማቆሚያ ግንባታዎችን የያዘ ሲሆን፥ ሁለቱ በእንጦጦ ፖርክ ዋና መግቢያ በር እንዲሁም ሶስተኛው በሱሉልታ መግቢያ በኩል የተገነቡ ናቸው፡፡
እነዚህ የመኪና ማቆሚያዎች 14 ሺህ 063 ሜትር ስኩዌር ስፋት ያላቸው ሲሆን፥ በአንድ ጊዜ 450 መኪኖችን ማቆም የሚያስችሉ ናቸው፡፡
የመኪና ማቆሚያ ሥፍራዎቹ በተለይም እንጦጦ ፖርክን ለመጎብኘት ለሚመጡ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የውጭ ቱሪስቶች ቆይታቸውን ምቹ እንደሚያደርግላቸው ተገልጿል።
በተጨማሪም በአካባቢው በቂ የመኪና ማቆሚያ በመኖሩ የተሳለጠ የትራፊክ ፍሰት እንዲኖር የሚያስችል መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.