በገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ የተመራ የልዑካን ቡድን በሳዑዲ ጉብኝት እያደረገ ነው
አዲስ አበባ፣ጥር 19፣2014 (ኤፍ ቢሲ) በኢፌዴሪ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ የልዑካን ቡድን ከትናንት ጀምሮ በሳዑዲ አረቢያ ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል።
የልዑካን ቡድኑ በሳዑዲ ቆይታው በሁለቱ አገራት የጋራ ጉዳዮች እና በዜጎች አያያዝ እንዲሁም በእስር ቤት ያሉ ኢትዮጵያዊያንን በተመለከተ እየመከሩ ነው።
በተጨማሪም በአገር ቤት ስለነበረው ጦርነት እና ወቅታዊ ሁኔታዎችን በተመለከተ ገለጻ ያደርጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ሪያድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን