ጂ ኤን ቢ የተሰኘው የቴክኖሎጂ ድርጅት በኢትዮጵያ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) መቀመጫውን ካሊፎርኒያ ያደረገው ጂ ኤን ቢ የተባለው የቴክኖሎጂ ድርጅት በኢትዮጵያ ምርታማነትን በሚያሳድጉ የቴክኖሎጂ ምርቶች ላይ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለፀ።
የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ኬን ሃሪሰን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዲኤታ ጀማል በከር ጋር ተወያይተዋል።
በውይይቱ ሚኒስትር ዲኤታው ኢትዮጵያ ቴክሎጂን በመጠቀም የምታመርታቸው ምርቶች ጥራታቸውን የጠበቁና በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል የሚደረገውን ጥረት ድርጅቱ እንዲደግፍ ጠይቀዋል።
በተለይ በግብርና ምርቶች ማቀነባበር ዘርፍ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም የአሰራር ስርዓት እንዲዘረጋ የሚደረገውን ጥረት ድርጅቱ እንዲያግዝም ነው የጠየቁት።
የድርጅቱ ፕሬዚዳንት ኬን ሃሪሰን በበኩላቸው ድርጅቱ በምግብና መጠጥ ማቀነባበር፣ የህክምና ግብዓቶች ምርት፣ በትራንስፖርት ዘርፍና በህዋ ምርምር እቃዎች ምርት ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገልፀዋል።
ድርጅቱ ጤንነቱ የተጠበቀ ምግብና መጠጥ ምርት ዘርፍ፣ በህክምናና የህክምና ግብዓቶች ምርት፣ በመጓጓዣ ዘርፍ፣ ለህዋ ሳይንስ ምርምር በሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችና በኤሌክትሪክ አስተላላፊ እቃዎች ምርት ላይ የተሰማራ መሆኑን ከኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision