Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል አዳባ ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን አዳባ ወረዳ በተከሰተ የትራፊክ አደጋ የ17 ሰዎች ሕይወት ማለፉን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡
አደጋው ዛሬ ከረፋዱ 4 ሰዓት አካባቢ በአዳባ ወረዳ ልዩ ስሙ ሰብስቤ ዋሻ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ነው የደረሰው፡፡
አደጋው የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሮቤ ከተማ ወደ ሻሸመኔ ሲጓዝ በስፍራው በመገልበጡ የደረሰ መሆኑን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.