Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ሐረርጌ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሆስፒታል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ኮምቦልቻ ወረዳ ከ300 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ሆስፒታል ለመገንባት የመሠረት ድንጋይ ተቀመጠ።

በውጪ አገራት የሚኖሩ ዳያስፖራዎች ናቸው ይህን ሆስፒታል የሚያስገነቡት።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ፈረሀን አህመድ እና የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነው የመሠረት ድንጋዩ የተቀመጠው።

የዳያስፖራው ማህበረሰብ ተወካይ አቶ ፈረሀን አህመድ፥ የሆስፒታሉ ግንባታ እስኪጠናቀቅ ሁሉም ድጋፉን ማድረግ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ጀማል ዩሱፍ በበኩላቸው፥ ሀገሪቱ ለምታ እና በልጽጋ ለማየት ጤናማ ማህበረሰብ መኖሩ አስፈላጊ በመሆኑ ሆስፒታሉ ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ እና አገልግሎት መስጠት በሚጀመርበት ጊዜም አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግ ገልጸዋል።

የሆስፒታሉ ግንባታ ተጠናቆ አገልግሎት መሰጠት በሚጀምርበት ጊዜ ከ1 ሚሊየን በላይ ለሚሆኑ የአከባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እንደሚሰጥ ተገልጿል።

በነሰሪ ዩሱፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.