Fana: At a Speed of Life!

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለ200 ሴቶች ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ከአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተማዎች ለተውጣጡ 200 ሴቶች ማዕድ አጋርቷል፡፡

ፈጠራ በታከለበት መንገድ እንዴት መሠረታዊ አትክልቶችን በየቤታችን ለማምረት እንደሚቻል የሚያሳዩ በቅጥር ጊቢው የሚከናወኑ የከተማ ግብርና ስራዎችም ተጎብኝተዋል፡፡

በስነ ስርዓቱ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ እና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬ÷ ቁሶችን መልሶ በጥቅም ላይ በማዋል የቦታ እጥረትን ቀርፎ የምንመገበውን ከደጃፋችን ማግኘትን ባህላችን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

የጓሮ ግብርናን በተመለከተ ሙያዊ እገዛ በክፍለ ከተማ፣ ወረዳና ቀበሌ ደረጃ ለማግኘት እንደሚቻልም አስታውቀው፤ ሁሉም ሰው በተነሳሽነትና በኃላፊነት ምግቡን ከደጁ ለማግኘት እንዲሠራ ማበረታታቸውን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.