Fana: At a Speed of Life!

ዳያስፖራው ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት ሚናውን  እንዲወጣ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች  ይፈጠራሉ– ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዳያስፖራው ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት ሚናውን እንዲወጣ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ እየተስተዋሉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት የተቋቋመው አገራዊ የምክክር ኮሚሽን የታለመለትን ግብ እንዲመታ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚጠበቅባቸውን ሚና ሊወጡ እንደሚገባ ኮሚሽኑ አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራዎችም ለአገራዊ ምክክሩ ስኬት የበኩላቸውን ሚና በመወጣት ለአገራዊ መግባባት አዎንታዊ አሻራቸውን ያሳርፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዶክተር ዮናስ አዳዬ ÷ የዳያስፖራው ማኅበረሰብ በአገራዊ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።

ለአብነትም በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ፣ በ”#በቃ” እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን ነው ያስታወሱት።

ይህንኑ አስተዋጽኦ በብሔራዊ ምክክሩ ላይ እንዲደግሙ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሁኔታዎችን ለማመቻቸት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ከጉዳዩ ጋር ተያይዞ ኮሚሽኑ አሁን ላይ ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቆ በዝግጅት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀትም በቀጣይ ከሕዝቡ ግብዓት ለማግኘት እየተሰራ መሆኑን ገልጸው÷እነዚህ ተግባራት ሲጠናቀቁም ወደ ትግበራ ምዕራፍ እንደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!፣

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.