በጋምቤላ ክልል በአንድ ጀምበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኝ ተተከለ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋምቤላ ክልል የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ገለጸ።
“ዐሻራችን ለትውልዳችን” በሚል መሪ ሀሳብ በአንድ ጀምበር 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል የታቀደ ሲሆን፥ ከ2 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉን የገለጸው የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ነው፡፡
በክልሉ ለተጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ውጤታማነት የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ሊጠናከር እንደሚገባም ተገልጿል፡፡
የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አጃክ ኡቻላ በዚሁ ወቅት÷በዘንድሮው ክረምት በክልሉ 9 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ ለመትከል ታቅዶ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ ብለዋል።
በአንድ ጀምበር ለመትከል ከተያዘው 1 ነጥብ 7 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር ውስጥ ከዕቅድ በላይ 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ችግኝ ተተክሏልም ነው ያሉት፡፡
የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩን ጨምሮ ከ2 ነጥብ 7 ሚሊየን በላይ ችግኝ መተከሉንም ገልጸዋል፡፡
በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እስካሁን በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አመራሩን ጨምሮ ከ57 ሺህ በላይ የሕብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!