10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት የፊታችን ነሐሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 10ኛው የበጎ ሰው ሽልማት ስነ ስርዓት የፊታችን ነሐሴ 29 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚካሄድ የበጎ ሰው ሽልማት በጎ አድራጎት ድርጅት አስታውቋል፡፡
ሽልማቱ ለሀገርና ለማህበረሰቡ አርአያነት ያለው ተግባር የፈፀሙ ኢትዮጵያውያን ዕውቅና የሚያገኙበት መሆኑም ተገልጿል፡፡
የበጎ ሰው ሽልማት ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ቀለመወርቅ ሚደቅሳ በሰጡት መግለጫ÷ የዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት በዘጠኝ ዘርፎች 700 እጩዎች ከየካቲት ሦስት እስከ መጋቢት ድረስ የእጩዎች ምርጫ በማድረግ ከየዘርፉ ሦስት ሦስት ሰዎች በአጠቃላይ 27 እጩዎች ለበጎ ሰው ሽልማት መቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡
በኪነ ጥበብ ዘርፍ፣ በመምህርነት፣ በሳይንስ፣ በጎ አድራጎት፣ ንግድና ሥራ ፈጠራ፣ መንግሥታዊ ተቋማት ኃላፊነት፣ ማህበራዊ ጥናት፣ ሚዲያና ጋዜጠኝነት እንዲሁም በቅርስና ባህል ዘርፍ ለአገሪቱ ዕድገት አስተዋጽዖ ያበረከቱ ኢትዮጵያውያንን በማካተት እውቅና እንደሚሰጥ አስታውቀዋል፡፡
የቀረቡ 27 እጩዎችም፡-
1. የኪነ ጥበብ (ፊልም ዳይሬክቲንግ) ዘርፍ እጩዎች
1.1. ሄኖክ አየለ
1.2. ዓለምፀሐይ በቀለ
1.3. አብርሃም ገዛኸኝ
2. የመምህርነት ዘርፍ እጩዎች
2.1.መ/ር ወልደሃና ወልደዮሐንስ
2.2. ዶ/ር ውብሸት ዠቅያለ
2.3. ፕ/ር እንድርያስ እሸቴ
3. የመንግሥታዊ የሥራ ኃላፊነት እጩዎች
3.1. አቶ ግርማ ዋቄ
3.2. ዶ/ር ዳንኤል በቀለ
3.3. አቶ ተስፋዬ ነዋይ
4. የሚዲያ ዘርፍ እጩዎች
4.1. ጋዜጠኛ ግርማ ፍሰሀ
4.2. አቶ ሰለሞን ገ/ሥላሴ
4.3. ሠይፉ ፋንታሁን
5. ቅርስና ባህል ዘርፍ እጩዎች
5.1.አቡ ገብሬ
5.2. ሐጂ መሀመድ አወል ሀምዛ
5.3. መ/ር ዜና ማርቆስ እንዳለው
6. በጎ አድራጎት ዘርፍ እጩዎች
6.1.አቶ ሚኪያስ ለሰሰ
6.2. ወ/ሮ ክብረ ከበደ
6.3. አቶ ሄኖክ ፈቃዱ
7. ንግድና ሥራ ፈጠራ ዘርፍ እጩዎች
7.1.አቶ ሰኢድ መሀመድ
7.2. አቶ ጠንክር ቴሪ
7.3. ዶ/ር ፍሰሀ እሸቱ
8. ዳያስፖራ ዘርፍ እጩዎች
8.1. ዶ/ር መንበረ አክሊሉ
8.2. ርብቃ ጌታቸው
8.3. አና ጌታነህ
9. የሳይንስ ዘርፍ እጩዎች
9.1. ፕ/ር ረዳ ተክለሃይማኖት
9.2. ዶ/ር ምትኬ ሞላ
9.3. ፕ/ር በላይ ወልደየስ
ከእነዚህ በተጨማሪም በድርጅቱ ቦርድ የሚመረጥ ልዩ ተሸላሚ እንደሚኖሩ ተገልጿል፡፡
በማህሌት ተ/ብርሃን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!