Fana: At a Speed of Life!

ኢኖቬሽን ከችግር የሚነሳ ሀሳብን ወደ ፋይዳ የመቀየር ሂደት በመሆኑ ዘርፉን ማሳደግ ይገባል -የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢኖቬሽን የሰው ልጆች የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ትርጉም ባለው መልኩ ጥቅም አንዲሰጡ የማድረግ ሂደት መሆኑን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

በሚኒስቴሩ የኢኖቬሽን ልማትና ምርምር ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሰላምይሁን አደፍርስ እንደገለጹት÷ ኢኖቬሽን እንደ ትምህርት፣ ጤና፣ ግብርና እና መሰል ከሀሳብ የሚነሱ ማህበራዊ ችግሮችን ለሰው ልጅ ትርጉም ባለው መልኩ ምርትና አገልግሎት የመቀየር ሂደት ነው፡፡

ኢትዮጵያ በኢኖቬሽን ዘርፍ በማደግ ላይ ካሉ አገራት የምትመደብ መሆኗን ጠቁመው÷ “ኢኖቬሽን ለልማት” በሚለው መርሐ ግብር መሠረት ዘርፉን ለማሳደግ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህም ኢትዮጵያ ደካማ የሆነውን የኢኖቬሽን ስነ ምህዳር ለማሳደግ በጥናት ላይ የተመሠረቱ የሕግ ማዕቀፎችና አሠራሮች እየለሙ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

በኢኖቬሽን ቴክኖሎጅ ከዳበረችው ከእስራኤል በተገኘ ተሞክሮ መሠረት አዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎች አዋጅና ሌሎች የሕግ ማዕቀፎች መዘጋጀታቸውን እና የቁጥጥር ስርዓትና አሠራሮች እየለሙ መሆኑንም ነው ገልጸዋል፡፡

በዚህም በአዳዲስ ሥራ ፈጣሪዎች እና ሌሎች የቴክኖሎጂ መሠረት ባላቸው የቢዝነስ ሞዴሎች አማካኝነት አካባቢያዊ ችግሮችን የሚፈቱ እንደ እንጀራ መጋገሪያ ማሽን ያሉ ውጤቶች ተገኝተዋል ብለዋል፡፡

ኢኖቬሽን ሚኒስቴር በኢትዮጵያ ዘርፉን ለማሳደግ የተለያዩ ተቋማት አዳዲስ አሠራሮችና የፈጠራ ሥራዎችን በድፍረትና በትዕግስት እንዲሞክሩ እገዛ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.