Fana: At a Speed of Life!

ፕሮፌሰር ብርሃኑ የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮን የለውጥ ስራዎች ጎበኙ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮን የለውጥ ስራዎች ጎብኝተዋል።
 
ሚኒስትሩ በጭፍራ ወረዳ በህወሓት ሽብር ቡድን የወደሙ ትምህርት ቤቶችን ለማስገንባት የመሰረት ድንጋይ ካስቀመጡ በኋላ በሰመራ የክልሉ ትምህርት ቢሮን ጎብኝተዋል።
 
በጉብኝታቸው ቢሮው ምቹ የስራ ሁኔታ ለመፍጠር የሰራቸውን ስራዎች እና አጠቃላይ በመማር- ማስተማር ስዋች ላይ ገለፃ ተደርጎላቸዋል።
 
በተጨማሪም ሚኒስትሩ እየተካሄደ የሚገኘውን የ2014 የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የእርማት ሂደት ጎብኝተዋል።
 
የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ አሊ መሀመድ÷ቢሮው ከማሻሻያው በኋላ የተገበራቸውን ዋና ዋና የለውጥ ሂደቶች ማብራራታቸውን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተለይም ጥሩ የስራ ከባቢን መፍጠርና የመማር- ማስተማር ስራው የተሳለጠ እንዲሆን ምቹ መደላድል መፈጠሩን ጠቁመው÷የትምህርት ሚኒስቴርም የክልሉን የመማር -ማስተማር ሂደት በተሻለ መልኩ ለማከናወን ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
 
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በበኩላቸው÷ወጣት አመራሮች ከለውጥ በኋላ ምቹ የስራ ከባቢን በመፍጠር የመማር-ማስተማር ሂደቱ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሄድ እያደረጉ ያለው ጥረት አበረታች መሆኑን ገልፀዋል።
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.