Fana: At a Speed of Life!

ዩኒሴፍ ለኢትዮጵያ የ5 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በኢትዮጵያ በግጭትና ድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ5 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ አስታውቋል፡፡
 
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ በኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ምክትል ዳይሬክተር ጄን ሙታን ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም የህጻናት እና የማህበራዊ ጥበቃ አሰራር ስርዓትን እንዲሁም ተቋማዊ አቅምን ማጎልበትና ማጠናከር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
ሚኒስትሯ ዩኒሴፍ ለሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በየዘርፉ ለሚከናወኑ ተግባራት እያደረገ ያለውን እገዛ አድንቀዋል፡፡
 
ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ በተከሰተው ድርቅ እና ግጭት ሳቢያ የተጎዱ ወገኖችን ለመታደግ ለሚደረገው ጥረት ስኬታማነት ሰብዓዊ ድጋፍን ጨምሮ ለአዕምሮ ጤናና ስነልቦና ጉዳት ለተጋለጡ ወገኖች ላደረገው የማህበራዊ ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
 
በቀጣይም በአፋር እና አማራ ክልሎች በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች እንዲሁም በኦሮሚያና በደቡብ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ምክትል ዳይሬክተር ጄን ሙታን በበኩላቸው÷ በሚኒስትሯ የቀረበውን ጥሪ በመቀበል የተቋሙን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ለማጎልበት የሚያስችሉ ሁለንተናዊ ድጋፎችን በይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልጸዋል::
 
ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ በግጭት እና በድርቅ ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚያስችል የ5 ነጥብ 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ እንደሚያደርግ ማስታወቃቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.