Fana: At a Speed of Life!

ብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት እያደረኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ሀገር ቤት እንዲገቡ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ የሚያስችል ፖሊሲ መዘጋጀቱን መናገራቸው ይታወሳል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት በብሔራዊ ባንክ ሱፐርቪዝን ዳይሬክተር ፍሬዘር አያሌው ÷ የውጭ የፋይናንስ ተቋማት ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ ጋር ለማጣጣም የሚያስችል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዝግጅቱ የህግ ማሻሻያ እና የቁጥጥር ስርዓት ለውጦችን ማድረግ የሚያስችሉ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

በባንኩ የክፍያ ሂሳብ ማወራረጃ ተጠባባቂ ዳይሬክተሩ ሰለሞን ዳምጠው በበኩላቸው÷ መሰል አዳዲስ አሰራሮች የክፍያ ስርዓቱን በማዘመን ከፍ ያለ አበርክቶ እንዳላቸው አስረድተዋል።

እንዲሁም ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የውጭ ምንዛሬን ለማሳደግ፣ በሀገር ውስጥ በማንኛውም ዘርፍ በቂ ብድር ለመስጠት ዕድል እንደሚፈጥር ፣ ዘርፉን የበለጠ ዘመናዊና ተወዳዳሪ ለማድረግና ተደራሽነትን አስተማማኝ ለማድረግ እንደሚያግዝ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል ካለፉት አራት ዓመታት ወዲህ የባንክ ዘርፍ እድገት እያመጣ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን÷ በዚህም ቁጥሩም ቀድሞ ከነበረው 18 ወደ 30 ከፍ ማለቱ ታውቋል፡፡

በተጨማሪም ብሄራዊ ባንክ ባዘጋጃቸው የተሻሻሉ አሰራሮች ምክንያት የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ቁጥር 40፣ የኢንቨስትመንት ተቋማት ቁጥር ደግሞ ከ18 በላይ መሆኑንም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

በኃይለየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.